Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 17 December 2011 10:38

የ”አፍሪካ ፋሽን ሳምንት” ከ3 ወራት በኋላ በአዲስ አበባ ይካሄዳል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

የ2012 የ”አፍሪካ ፋሽን ሳምንት” ከሦስት ወራት በኋላ በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ተገለፀ፡፡ አዘጋጆቹ ለአዲስ አድማስ በላኩት መግለጫ እንዳመለከቱት፤ የፋሽን ሳምንቱ የዲዛይነሮች ውድድር፤ የንግድ ኤክስፖ፤ ሲምፖዚዬም፤ ዎርክሾፕና የጥበብ ትእይንቶችን ያካትታል፡፡ በዝግጅቱ ላይ ከመላው አለም የተሰባሰቡ ምርጥ የፋሽን ዲዛይነሮች፤ ሞዴሎችና ትላልቅ ኩባንያዎች እንደሚሳተፉም ይጠበቃል፡፡ በዲዛይነሮች መካከል የሚካሄድ ትልቅ ውድድር እንደሚኖር የጠቆሙት አዘጋጆቹ፤ ሦስት ከፍተኛ ሽልማቶች እንደተዘጋጁም አስታውቀዋል፡፡  የፋሽን ሳምንቱ ሰሞኑን በጁፒተር ኢንተርናሽናል ሆቴል በሚካሄድ ዎርክሾፕ እና በትሮፒካል ጋርደን በሚቀርብ የፋሽን ሾው ዝግጅት ይካሄዳል ተብሎ የነበረ ሲሆን የፕሮግራም ለውጥ ተደርጐ ከ3 ወራት በኋላ እንዲካሄድ መወሰኑን አዘጋጆቹ በመግለጫቸው አስታውቀዋል፡፡   ”ኦሪጅን አፍሪካ” እና “ኤሲቲአይኤፍ” ከተባሉ ድርጅቶች ጋር ባደረጉት አዲስ ስምምነትም  አዳዲስ ዝግጅቶች ለማካተት እንደታቀደ ተገልጿል፡፡

 

 

Read 1914 times Last modified on Saturday, 17 December 2011 10:45