Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 17 December 2011 10:34

“ሁለተኛው ሰማይ”፣ “ገንዘብና ጭንቀት”፣ “ለገሃነም ፀሎት” ለሕትመት በቁ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

“ዜማ ብዕር” ለአምስተኛ ጊዜ ተመረቀ

ኬሚካል ኢንጂነር መልካም ሰው አባተ ያዘጋጀው “ሁለተኛው ሰማይ” ሳይንሳዊ ረዥም ልቦለድ ለንባብ በቃ፡፡ መታሰቢያነቱን ለቀድሞዋ ኢትዮጵያ ያደረገው መፅሐፍ 272 ገፅ አለው፡፡ በሀገር ውስጥ 35 ብር በውጭ ሀገራት በ15 ዶላር እየተሸጠ ነው፡፡ “ምስጢረ ሄዋን” የሚል የሴቶች ሥነልቦና መፅሐፍ ለንባብ አብቅቶ የነበረው ኢንጂነር መልካም ሰው በ”ሜዲካል” እና በቀድሞ የ”ጐግል” ጋዜጠኝነቱም ይታወቃል፡፡በዳንኤል ዓለሙ የተዘጋጀው “የገንዘብ እና ጭንቀት” መፅሐፍ ታትሞ ለገበያ ቀረበ፡፡ 13 ብር እና 5 ዶላር እየተሸጠ ያለው መፅሐፍ 48 ገፆች አሉት፡፡ ዳንኤል ካሁን ቀደም በተመሳሳይ መልኩ “የጓደኝነት ምስጢር” የትርጉም ሥራ፣ “ቅናትና ምቀኝነት” እንዲሁም “የእውነት መንገድ” የተሰኙ መፃሕፍት አስነብቧል፡፡“ለገሃነም ፀሎት” ክፍል ሁለት የረዥም ልቦለድ መፅሐፍ ታትሞ ሰሞኑን ለንባብ በቃ፡፡ ነዋሪነቱን አሜሪካ ያደረገው ደራሲ ጭብጡን እዚያ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዙሪያ ያደረገው የደራሲ ግዛቸው ገብረእግዚአብሄር መፅሐፍ በሦስት ክፍል የተዘጋጀ ሲሆን ክፍል ሦስቱ ገና ለንባብ አልበቃም፡፡ 264 ገፆች ያሉት ክፍል ሁለት መፅሐፍ በውጨ ሀገራት 15 ዶላር በሀገር ውስጥ 40 ብር እየተሸጠ ነው፡፡ይህ በዚህ እንዳለ “ዜማ ብዕር ኢትዮጵያ የሴቶች የሥነፅሁፍ ማህበር “ዜማ ብዕር” ቁጥር አንድ እና ቁጥር ሁለት መፃሕፍቱን ለአምስተኛ ጊዜ ነገ በአዲስ አበባው ዋቢ ሸበሌ ሆቴል ያስመርቃል፡፡ መፃህፍቱ ካሁን ቀደም በመቀሌ፣ በባህርዳር፣ በጐንደር እና ደብረማርቆስ ከተሞች ተመርቀዋል፡፡

 

 

Read 2261 times Last modified on Saturday, 17 December 2011 10:43