ለ14ኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የፊታችን ሰኞ ምዝገባው ሊጀመር ነው፡፡ ከስድስት ወር በኋላ በአዲስ አበባ በሚካሄደው የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫው ላይ ተሳታፊዎች 40ሺ እንደሚሆኑ ይጠበቃል፡፡
የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አዘጋጆች እንዳስታወቁት ለ14ኛው የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ውድድር ሰኞ እለት በተመረጡ ስምንት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ መስርያ ቤቶች ምዝገባው የሚጀመር ሲሆን ለመጀመርያዎቹ 1ሺ ተመዝጋቢዎች የልምምድ ቲሸርት እንደሚሰጥ ገልፀዋል፡፡
በሌላ በኩል በነገው እለት ከሚደረገው የቀለበት መንገድ የዱላ ቅብብል ጋር ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ያዘጋጃቸው ውድድሮች ብዛት 100 ደርሰዋል፡፡
Published in
ስፖርት አድማስ