Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 17 December 2011 10:01

የሼርሎክ ሆምስ ፊልሞች አትራፊ ሆነዋል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ከ84 ዓመታት በፊት የተፃፉት የሼርሎክ ሆምስ ገድሎችን የሚተርኩት የሰር አርተር ኮናን ዶይል ልቦለድ መፃህፍት በፊልም ስራ አትራፊ እንደሆኑ ቢቢሲ ዘገበ፡፡ ከወር በኋላ በመላው ዓለም ለእይታ የሚበቃው አዲሱ የሼርሎክ ሆምስ ፊልም “ኤ ጌም ኦፍ ሻዶውስ” የሚሰኝ ሲሆን የፊልሙ ዲያሬክተር እንግሊዛዊው ጋይ ሪቼ እንደሆነ ታውቋል፡፡ በመሪ ተዋናይነት ሮበርት ጉዲንግ ጁኒዬርና አሽሊ ጁድ ይሳተፋሉ ተብሏል፡፡ የሼርሎክ ሆምስ ገድሎችን የሚተርኩ 56 አጭር ልቦለዶችና አራት መለስተኛ የልቦለድ መፅሃፍት ሲኖሩ እስካሁን 200 የሚደርሱ ፊልሞች እንደተሰሩባቸው ታውቋል፡፡በተያያዘ የፈረንጆች ገና እና የአዲስ ዓመት በዓላትን አስመልክቶ በቀጣዩ ሳምንታት ከ16 በላይ  ፊልሞች ለዕይታ እንደሚቀርቡ ሮይተርስ አመለከተ፡፡ ሰሞኑን በዱባይ ኢንተርናሽናል ፊልም ፌስቲቫል ላይ የተመረቀውን የቶም ክሩዝ “ሚሽን ኢምፖስብል 4” ጨምሮ በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት በ100 ሚሊዮን ዶላር የተሰሩት ሁለት የስፒልበርግ ፊልሞች “ቲንቲን” እና “ዋር ሆርስ” እንዲሁም “አልቪን ኤንድ ቻምፒኪንስ” የተሰኙ ፊልሞች ለተመልካች ይቀርባሉ ተብሏል፡፡ በ2012 ደግሞ የ”ቦርን”፤ የ”ቦንድ”ና እና የ”ባትማን” ተከታታይ አዳዲስ ፊልሞች ለእይታ እንደሚበቁ ይጠበቃል፡፡

Read 2843 times