Print this page
Monday, 19 May 2014 09:14

ኢትዮጵያ የምግብ ዋስትና አለማቀፍ ጉባኤ እያስተናገደች ነው

Written by 
Rate this item
(0 votes)

           ኢትዮጵያ በአለማቀፍ ደረጃ ለሚከሰቱ የርሃብና የድህነት ቀውሶች ተገቢ መፍትሄ የማፈላለግ ዓላማ ያለውንና በአለማቀፍ የምግብ ፖሊሲ ምርምር ኢንስቲቲዩት የተዘጋጀውን ‘2020 ቢልዲንግ ሪሳይለንስ ፎር ፉድ ኤንድ ኒዩትሪሽን ሴኪዩሪቲ’ የተሰኘ አለማቀፍ የምግብ ዋስትና አቅም ግንባታ ፖሊሲ የምክክር ጉባኤ እያስተናገደች ነው። ፖሊሲ አውጪዎችን፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን፣ የግሉን ሴክተር፣ ተመራማሪዎችንና ማህበረሰቡን በምግብ ደህንነት ዙሪያ መረጃ ለመስጠት፣ ተጽእኖ ለመፍጠርና ጉዳዩን ቀዳሚ አጀንዳቸው አድርገው እንዲንቀሳቀሱ አለማቀፍ ንቅናቄን ለመፍጠር በሚያስችል መልኩ የተዘጋጀ ነው የተባለው ይህ አለማቀፍ የፖሊሲ ምክክር ጉባኤ፤ በዘርፉ ያንዣበቡ አደጋዎችን ለይቶ በማውጣት በጋራ የሚመከርበት፣ መፍትሄዎች የሚመነጩበት፣ ክፍተቶች የሚለዩበትና ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችሉ የድርጊት መርሃግብሮች የሚቀረጹበት ነው ተብሏል።

ፖሊሲዎችን፣ ኢንቨስትመንቶችንና ተቋማትን በማሻሻል በአለማቀፍ ደረጃ የምግብ ደህንነትን ማጠናከር በሚቻሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ በሚመክረው ኢትዮጵያ የምግብ ዋስትና አለማቀፍ ጉባኤ እያስተናገደች ነው አለማቀፍ ጉባኤ ላይ፣ በተለያዩ ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ የሚያጠነጥኑ 28 ያህል የጥናት ወረቀቶች የሚቀርቡ ሲሆን በአለማቀፍ ደረጃ ታዋቂነትን ያተረፉ 140 ባለሙያዎችና ተመራማሪዎችም በጉዳዩ ዙሪያ ማብራሪያ ይሰጣሉ። በጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ እና በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ንኮሳዛና ድላሚኒ ዙማ ንግግር፣ ከትናንት በስቲያ በሸራተን አዲስ የተከፈተውና ከተለያዩ የአለም አገራት የተውጣጡ ከ800 በላይ በምግብ፣ በጤና፣ በግብርና፣ በሰብአዊ ተግባራትና ከልማት ጋር በተያያዙ ሌሎች ዘርፎች የተሰማሩ ባለሙያዎችና የሚመለከታቸው አካላት ተወካዮች እየተሳተፉበት የሚገኘው ይህ አለማቀፍ ጉባኤ፣ ዛሬ ምሽት ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።

Read 1892 times
Administrator

Latest from Administrator