Saturday, 17 December 2011 08:59

የኢህአዴግ ስንፍና ራሱን ከደርግ ጋር ማወዳደሩ! “ማንን ታሸንፋለህ ቢሉት ሚስቴን”

Written by  አልአዛር ኬ
Rate this item
(0 votes)

 

ኢህአዴግ ለአመታት የተጠናወተውን ይህን አጓጉል ልማድ የምንተቸው በጥላቻ አሊያም በቅናትና በምቀኝነት ተነሳስተን ሳይሆን ቀደም ብለን በጠቀስነው ምክንያት የተነሳ ብቻ ነው፡፡ በእርግጥም ኢህአዴግ ከደርግ ጋር የያዘውን ድርቅ ያለና አሳዛኝ ፉክክር ላስተዋለ ድርጊቱ አስገራሚም አሳዛኝም መሆኑን በቀላሉ መገንዘብ ይቻለዋል፡፡
ኢህአዴግ የመንግስትነት ስልጣን ከያዘበት ካለፉት ሀያ አመታት ጀምሮ ዳግመኛ ተመልሶ እንዳያንሠራራ አድርጌ አሸንፌዋለሁ እያለ ከሚሸልልበት የደርግ ስርአት ጋር ያላባራና ምናልባትም የወደፊት መጨረሻው የማይታወቅ ታላቅ ፉክክር የመግጠሙ ሁኔታ “ማንን ታሸንፋለህ ቢሉት ሚስቴን” አለ የተባለውን ሠውዬ ታሪክ ያስታውሠናል፡፡ ሠውየው በዚህች አለም የሚያሸንፈው ሰው ቢኖር ሌላ ሳይሆን ሚስቱ ብቻ ናት፡፡ ኢህአዴግም ከሱ የተሻልኩ መንግስት ነኝ እያለ የሚሸልልበት አካል ሌላ ሳይሆን  የደርግ መንግስት ብቻ ሆኗል፡፡
ለመሆኑ ኢህአዴግ እንዲህ ላለው መጥፎ አባዜ የተዳረገው በምን ምክንያት ነው? ከኢህአዴግ ያለፈ ታሪክና ነገረ ስራ በመነሳትም ለዚህ ጥያቄ የሚሆኑ መልሶችን  መዘርዘር ቢቻልም ጉዳዩን አጠቃሎ ማቅረብ ይቻላል፡፡ ቤቱ ውስጥ ካለችው ሚስቱ ውጭ መመልከት አቅቶት ወይም ባለመፈለግ የማሸንፈው ሚስቴን ብቻ ነው እንዳለው ሞኛሞኝ ሠውየ፣ ኢህአዴግም በፖለቲካ ጨዋታው ህግም ሆነ በመጫወቻ ሜዳው ጨርሶ በአቻነት ሊፎካከረው ከማይገባው ከደርግ ስርአት ሌላ አቻ ተፎካካሪ ፈልጐ ለመወዳደር አቅቶት ወይም ፍላጐት በማጣቱ ወይም ደግሞ ራሱን ገድዬ ቀብሬዋለሁ ከሚለው ከደርግ ስርአት ጋር በአቻነት በማስቀመጥና ከደርግ ሌላ የምፎካከረው መንግስት የለም ብሎ በማመኑ ነው፡፡  ይህ የኢህአዴግ ድርጊት አስገራሚና አስደናቂም ነው ያልነውም ለዚህ ነው፡፡
ኢህአዴግ ራሱን ሊያወዳድረው ከማይገባው ከደርግ ስርአት ጋር በማወዳደር ራሱን የተሻለ መንግስት አድርጐ፣ “ጉሮ ወሸባዬ”ና “ማታ ነው ድሌ” ፉከራ ለማቅረብ የሚያደርገው ጥረት የሚያረጋግጥልን አንድ ነገር ብቻ ነው - ኢህአዴግ የአላማና የግብ መለኪያ ሚዛኑ የደርግ መንግስት መሆኑና ገድዬ ቀብሬዋለሁ ብሎ ካወጀ ከሃያ አመታት በኋላም ደርግን ገድሎ ለመቅበሩ እርግጠኛ ባለመሆኑ ከደርግ ጣዕረሞት ጋር ሀይለኛ ግብግብ መግጠሙን፡፡
እንዲህ ባይሆን ኖሮማ ኢህአዴግ መስፈሪያ ሚዛኑን በመቀየር ፉክክሩን ከሌሎች የተሻሉ መንግስታት ጋር ያደርግ ነበር፡፡ ኢህአዴግ ላለፉት ሃያ አመታት በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ በማህበራዊ ኑሮና በሌሎችም መስኮች ያከናወናቸውን ስራዎች ከደርግ ጋር እያወዳደረ ራሱን የተሻለ መንግስት አስመስሎ ለማቅረብ ዘወትር በመሞከሩ ሊያፍርበት ይገባል፡፡ እንዴት ቢባል? ኢህአዴግ አራምደዋለሁ የሚለው የፖለቲካ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ፖሊሲና አሠራር ደርግ ይከተለው ከነበረው ፖሊሲና አሠራር ጋር ጨርሶ ሊወዳደር የሚችል ጉዳይ ባለመሆኑ ነው፡፡ የደርግን የፖለቲካ ስርአት ከኢህአዴግ የፖለቲካ ስርአት ጋር ከራሱ ከኢህአዴግ በስተቀር ማን ሊያወዳድር ይችላል? የኢህአዴግን የኢኮኖሚ ስርአት ከደርግ የኢኮኖሚ ስርአትስ ጋር ማን ማወዳደር ይችላል? ይህን እያደረገ ካለው ከኢህአዴግ በስተቀር፡፡
የደርግ ስርአት ሁኔታና ጉድለቶቹ በሚገባ ስለሚታወቁ ስርአቱ የሰው ልጆች ድንገት በጉልበት የሚጫንባቸው እንጂ በፈቃዳቸው ሊተዳደሩበት የሚመርጡትን የመንግስት ስርአት እንዳልሆነ ለማንም ግልጽ ነው፡፡ ይህንን ግልጽ ጉዳይ እስካሁን በትክክል መረዳት ያቃተው ኢህአዴግ ብቻ ነው፡፡ ራሱን ከደርግ ጋር እያወዳደረ በፕሮፖጋንዳ የሚደክመውና ለማሳመንም የሚጥረው እኛን ሳይሆን ገድዬ ቀበርኩት የሚለውን የደርግን ጣዕረሞት ነው ያልነውም በዚህ ምክንያት ነው፡፡
ኢህአዴግ ራሱን በደርግ መስፈሪያ እየለካ ባደረጋት እያንዳንዷ ነገር ሁሉ “ከደርግ የተሻልኩ መንግስትነቴን አውቃችሁ “አጨብጭቡልኝ” ማለቱ በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚና በማህበራዊ ጉዳዮች አስተሳሰብና አመለካከት እየመራሁት ነው ከሚለው ህዝብ በሰፊ ርቀት ተበልጦ ወደ ኋላ መጐተቱን ብቻ ሳይሆን ስንፍናውንም ያሳያል፡፡ ይሄ ስንፍናው ደግሞ የህዝቡን ስሜትና ፍላጐት በቅጡ እንዳይረዳ እንቅፋት ሆኖበታል፡፡
የኢህአዴግን አላውቅም እንጂ የኢትዮጵያ ህዝብ ደርግ እንደወደቀ ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ ስለዚህ የህዝቡ ፍላጐት ኢህአዴግ ከደርግ ጣዕረሞት ጋር ግብግብ እንዲገጥም ሳይሆን ራሱን ከሌሎች ዲሞክራቲክ ሀገራት ጋር እንዲያወዳድርና ጉድለቶችን እንዲሞላ ነው፡፡
በግንቦት ሀያ በአል ሰሞን የደርግን መውደቅና በደርግ መቃብር ላይ አዲሲቷ ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ እንደተገነባች ኢህአዴግ ሳይታክት ይነግረናል፡፡ የዲሞክራሲ መብቱ ኢህአዴግ እንደሚያወራው በተግባርም ይረጋገጥልኝ የሚል ነው፡፡ እንደአለመታደል ሆኖ ኢህአዴግ ግን አልገባውም፡፡
በዘንድሮ የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች በዓል ላይም ኢህአዴግ የተጨበጨበለት ዲሞክራሲያዊ ህገመንግስት ማጽደቁንና ከደርግ በበለጠ ለህዝቦች እኩልነትና መብት እውቅና መስጠቱን ሊያስረዳን በእጅጉ ሞክሯል፡፡ ሆኖም እኛ ይህን በሚገባ እናውቃለን፡፡  የእኛ ጥያቄ ተግባራዊ አፈፃፀሙ ላይ ነው፡፡ ይሄን ግን ፈጽሞ የተረዳ አይመስልም - ኢህአዴግ፡፡
አሁን ኢህአዴግ የዛሬ ሃያ አመት ጥየዋለሁ ከሚለው ከደርግ ጣዕረሞት ጋር የምናብ ትንቅንቁን እርግፍ አድርጐ ትቶ ራሱን ከሌሎች ዲሞክራሲያዊ ሀገራት ጋር ማወዳደር መጀመር አለበት፡፡
በዲሞክራሲ ግንባታ በኢኮኖሚና በማህበራዊ ኑሮ የረጅም ዘመን ልምድ ካላቸው የአሜሪካና የአውሮፓ ሀገራት ጋር ኢህአዴግ ራሱን እንዲያወዳድር ባናጨናንቀው እንኳ (አቻው ስላልሆኑ) ቢያንስ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ ውጤት ካስመዘገቡት እንደ ጋና፣ ሞሪሽየስና የመሳሰሉት የአፍሪካ ሀገራት ጋር ራሱን በማወዳደር ያሉበትን በርካታ ጉድለቶች እንዲሞላ እንመኛለን፡፡
ዲሞክራሲያዊ ህገመንግስት ማጽደቅና ለህዝቦች መብትና እኩልነት እውቅና መስጠት ብቻውን አንድን ሀገርና መንግስት ከሌላው የተሻለ ዲሞክራሲያዊ መንግስት ነው እንደማያስብለው ለማናችንም ቢሆን ግልጽ ነው፡፡ ዋናው ቁምነገሩ ያለው በተግባር መተርጐሙ ላይ ነው፡፡ የኢህአዴግ በርካታ ጉድለቶች ያሉት ደግሞ ተግባር ላይ ነው፡፡ (እሱ ራሱ ችግሬ አፈፃፀም ላይ ነው እንደሚለው) ስለዚህ የፕሮፓጋንዳው ቀረርቶና ያለአቻው ፉክክሩ  ቀርቶ የሚያወራውን በተግባር እንዲያሳየን በአክብሮት እናሳስበዋለን፡፡ ያለአቻ ፉክክር ትዝብት ላይ ከመጣል በቀር የትም እንደማያደርስ ማወቅ ብልህነት ነው፡፡

ኢህአዴግ ስልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ እንደ በአለ ሲመት የሚቆጠረውን የግንቦት 20ን በአል በየዓመቱ በተለያየ ሁኔታ እያከበርነው ኖረናል፡፡ መቼም እንኳን እንዲህ ያለ ሀገራዊ ዳራ ያለውን በአል ይቅርና የጐረቤት ልጅ የልደት በአልንም ቢሆን የምናከብረው እንደየግል ስሜታችን መሆኑ ይታወቃል፡፡ የግንቦት 20 በዓል ዋና ፈጣሪና ግንባር ቀደም አጋፋሪ የሆነው ኢህአዴግ፤ በዚህ በአል አከባበር ዙሪያ ከሚያደርጋቸው በርካታ ዝግጅቶች የፕሮጋንዳ ቅስቀሳ ዘመቻ ዋነኛው ነው፡፡

በበአሉ ሠሞን ኢህአዴግ እንደአሻው በሚቆጣጠራቸው የህዝብ መገናኛ አውታሮች ሲያቀርብልን የኖረው የፕሮፓጋንዳ ቅስቀሳ የትኛውን ወገን ለማሸነፍ ታልሞ እንደተሠራ ማወቅ ደግሞ ከባድ አይደለም፡፡ የቅስቀሳዎቹ ዋነኛ አላማ፤ ኢህአዴግ በህዝባዊ ድጋፍ ከጣለው ከደርግ ስርአት እጅግ  የተሻለ የፖለቲካ ድርጅትና መንግስት መሆኑን እየደጋገሙ ማስረዳት ሲሆን እነዚህ የፕሮፓጋንዳ ዝግጅቶች ሆነ ተብለው ታስበውና ታቅደው የተዘጋጁትም እኛን ሳይሆን ሞቶ የተቀበረውን የደርግን ጣዕረሞት ለማሸነፍ ብቻ ነው፡፡ልክ እንደ ግንቦት ሀያው በአል ሁሉ በተለይ ከባለፉት አራትና አምስት አመታት ወዲህ ኢህአዴግ በአዋጅ የተደነገገ ብሔራዊ በአል ከማድረግ በመለስ ትልቅ ትኩረት በመስጠት፤  በታላቅ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻና ሽርጉድ በየአመቱ ህዳር ሀያ ዘጠኝ ቀን እንድናከብረው የፈጠረልን ትልቅ በዓል አለ- የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦች ህዝቦች በአል፡፡

ባለፈው አርብ እለትም የአመቱ ተረኛ አዘጋጅ የሆነችው የትግራይዋ “ሠሜናዊት ኮከብ” የመቀሌ ከተማ በሺ የሚቆጠሩ እንግዶቿን ተቀብላ ድል ባለ ዝግጅት የአመት ተራዋን ተወጥታለች፡፡

ልክ በግንቦት ሀያ በአል ጊዜ ኢህአዴግ ደርግን ለመጣል የታገለውን ትግልና የከፈለውን መስዋዕትነት በማስመልከት እንደሚያስተላልፈው የተለያዩ የፕሮፓጋንዳ ዝግጅቶች ሁሉ  በዚህም በአል ሠሞን ሲቀሠቅሠንና ራሱን ሲሸጥልን ሰንብቷል፡፡

በእነዚህ ዝግጅቶችም ቢሆን ኢህአዴግ ሊያስተላልፈው የፈለገው አንድና ዋነኛ መልእክት፤ ዲሞክራሲያዊ ህገ መንግስት በማጽደቅና ለሀገሪቱ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች መብትና እኩልነት ህገመንግስታዊ እውቅናና ጥበቃ በመስጠት፣ ከደርግ ስርአት የተሻልኩ ወይም የበለጥኩ ነኝ የሚል ነው፡፡ ልክ እንደ ግንቦት ሀያው በአል የዚህም መልእክት ዋነኛው ግቡም እኛን ሳይሆን የደርግን ጣዕረ ሞት ለማሸነፍ የታለመ ይመስላል፡፡በመንግስታት የመምጣትና የመሄድ የፍርርቅ ሂደት ውስጥ አንዱ አዲስ መጤ መንግስት በተለያዩ ጊዜና አጋጣሚ ከሸኘው ወይም ከተካው መንግስት ራሱን የተሻለ መንግስት አድርጐ የማቅረቡ የፖለቲካ ጨዋታ፣ በየትኛውም የአለማችን አህጉር በየትኛውም ጊዜ የነበረና ምናልባትም ወደፊት የሚኖር ፖለቲካዊ ሂደት ነው፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ ታዲያ መንግስታቶቹ ይህን የሚያደርጉት አቻዬ ነው ከሚሉት መንግስት እና በእኩል የመጫወቻ ሜዳ ላይ ሆነው ነው፡፡ ለምን ቢባል? የእኔ መንግስት ከእከሌ  መንግስት የተሻለ ነው ብሎ ለማወዳደር ቢያንስ የመወዳደሪያ መመዘኛዎቹ ለሁለቱ ተፎካካሪዎች እኩል የሚሠሩ መሆን የግድ ይጠበቅባቸዋል፡፡ በሌላ አነጋገር ሁለት መንግስታት በተለያየ መስፈሪያ ተመዝነው ሊፎካከሩና አንዱ ካንደኛው የተሻልኩ ነኝ በሚል ሊሸልል አይችልም እንደማለት ነው፡፡ኢህአዴግ ለአመታት የተጠናወተውን ይህን አጓጉል ልማድ የምንተቸው በጥላቻ አሊያም በቅናትና በምቀኝነት ተነሳስተን ሳይሆን ቀደም ብለን በጠቀስነው ምክንያት የተነሳ ብቻ ነው፡፡ በእርግጥም ኢህአዴግ ከደርግ ጋር የያዘውን ድርቅ ያለና አሳዛኝ ፉክክር ላስተዋለ ድርጊቱ አስገራሚም አሳዛኝም መሆኑን በቀላሉ መገንዘብ ይቻለዋል፡፡ኢህአዴግ የመንግስትነት ስልጣን ከያዘበት ካለፉት ሀያ አመታት ጀምሮ ዳግመኛ ተመልሶ እንዳያንሠራራ አድርጌ አሸንፌዋለሁ እያለ ከሚሸልልበት የደርግ ስርአት ጋር ያላባራና ምናልባትም የወደፊት መጨረሻው የማይታወቅ ታላቅ ፉክክር የመግጠሙ ሁኔታ “ማንን ታሸንፋለህ ቢሉት ሚስቴን” አለ የተባለውን ሠውዬ ታሪክ ያስታውሠናል፡፡ ሠውየው በዚህች አለም የሚያሸንፈው ሰው ቢኖር ሌላ ሳይሆን ሚስቱ ብቻ ናት፡፡ ኢህአዴግም ከሱ የተሻልኩ መንግስት ነኝ እያለ የሚሸልልበት አካል ሌላ ሳይሆን  የደርግ መንግስት ብቻ ሆኗል፡፡

ለመሆኑ ኢህአዴግ እንዲህ ላለው መጥፎ አባዜ የተዳረገው በምን ምክንያት ነው? ከኢህአዴግ ያለፈ ታሪክና ነገረ ስራ በመነሳትም ለዚህ ጥያቄ የሚሆኑ መልሶችን  መዘርዘር ቢቻልም ጉዳዩን አጠቃሎ ማቅረብ ይቻላል፡፡ ቤቱ ውስጥ ካለችው ሚስቱ ውጭ መመልከት አቅቶት ወይም ባለመፈለግ የማሸንፈው ሚስቴን ብቻ ነው እንዳለው ሞኛሞኝ ሠውየ፣ ኢህአዴግም በፖለቲካ ጨዋታው ህግም ሆነ በመጫወቻ ሜዳው ጨርሶ በአቻነት ሊፎካከረው ከማይገባው ከደርግ ስርአት ሌላ አቻ ተፎካካሪ ፈልጐ ለመወዳደር አቅቶት ወይም ፍላጐት በማጣቱ ወይም ደግሞ ራሱን ገድዬ ቀብሬዋለሁ ከሚለው ከደርግ ስርአት ጋር በአቻነት በማስቀመጥና ከደርግ ሌላ የምፎካከረው መንግስት የለም ብሎ በማመኑ ነው፡፡  ይህ የኢህአዴግ ድርጊት አስገራሚና አስደናቂም ነው ያልነውም ለዚህ ነው፡፡

ኢህአዴግ ራሱን ሊያወዳድረው ከማይገባው ከደርግ ስርአት ጋር በማወዳደር ራሱን የተሻለ መንግስት አድርጐ፣ “ጉሮ ወሸባዬ”ና “ማታ ነው ድሌ” ፉከራ ለማቅረብ የሚያደርገው ጥረት የሚያረጋግጥልን አንድ ነገር ብቻ ነው - ኢህአዴግ የአላማና የግብ መለኪያ ሚዛኑ የደርግ መንግስት መሆኑና ገድዬ ቀብሬዋለሁ ብሎ ካወጀ ከሃያ አመታት በኋላም ደርግን ገድሎ ለመቅበሩ እርግጠኛ ባለመሆኑ ከደርግ ጣዕረሞት ጋር ሀይለኛ ግብግብ መግጠሙን፡፡

እንዲህ ባይሆን ኖሮማ ኢህአዴግ መስፈሪያ ሚዛኑን በመቀየር ፉክክሩን ከሌሎች የተሻሉ መንግስታት ጋር ያደርግ ነበር፡፡ ኢህአዴግ ላለፉት ሃያ አመታት በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ በማህበራዊ ኑሮና በሌሎችም መስኮች ያከናወናቸውን ስራዎች ከደርግ ጋር እያወዳደረ ራሱን የተሻለ መንግስት አስመስሎ ለማቅረብ ዘወትር በመሞከሩ ሊያፍርበት ይገባል፡፡ እንዴት ቢባል? ኢህአዴግ አራምደዋለሁ የሚለው የፖለቲካ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ፖሊሲና አሠራር ደርግ ይከተለው ከነበረው ፖሊሲና አሠራር ጋር ጨርሶ ሊወዳደር የሚችል ጉዳይ ባለመሆኑ ነው፡፡ የደርግን የፖለቲካ ስርአት ከኢህአዴግ የፖለቲካ ስርአት ጋር ከራሱ ከኢህአዴግ በስተቀር ማን ሊያወዳድር ይችላል? የኢህአዴግን የኢኮኖሚ ስርአት ከደርግ የኢኮኖሚ ስርአትስ ጋር ማን ማወዳደር ይችላል? ይህን እያደረገ ካለው ከኢህአዴግ በስተቀር፡፡የደርግ ስርአት ሁኔታና ጉድለቶቹ በሚገባ ስለሚታወቁ ስርአቱ የሰው ልጆች ድንገት በጉልበት የሚጫንባቸው እንጂ በፈቃዳቸው ሊተዳደሩበት የሚመርጡትን የመንግስት ስርአት እንዳልሆነ ለማንም ግልጽ ነው፡፡ ይህንን ግልጽ ጉዳይ እስካሁን በትክክል መረዳት ያቃተው ኢህአዴግ ብቻ ነው፡፡ ራሱን ከደርግ ጋር እያወዳደረ በፕሮፖጋንዳ የሚደክመውና ለማሳመንም የሚጥረው እኛን ሳይሆን ገድዬ ቀበርኩት የሚለውን የደርግን ጣዕረሞት ነው ያልነውም በዚህ ምክንያት ነው፡፡ኢህአዴግ ራሱን በደርግ መስፈሪያ እየለካ ባደረጋት እያንዳንዷ ነገር ሁሉ “ከደርግ የተሻልኩ መንግስትነቴን አውቃችሁ “አጨብጭቡልኝ” ማለቱ በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚና በማህበራዊ ጉዳዮች አስተሳሰብና አመለካከት እየመራሁት ነው ከሚለው ህዝብ በሰፊ ርቀት ተበልጦ ወደ ኋላ መጐተቱን ብቻ ሳይሆን ስንፍናውንም ያሳያል፡፡ ይሄ ስንፍናው ደግሞ የህዝቡን ስሜትና ፍላጐት በቅጡ እንዳይረዳ እንቅፋት ሆኖበታል፡፡የኢህአዴግን አላውቅም እንጂ የኢትዮጵያ ህዝብ ደርግ እንደወደቀ ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ ስለዚህ የህዝቡ ፍላጐት ኢህአዴግ ከደርግ ጣዕረሞት ጋር ግብግብ እንዲገጥም ሳይሆን ራሱን ከሌሎች ዲሞክራቲክ ሀገራት ጋር እንዲያወዳድርና ጉድለቶችን እንዲሞላ ነው፡፡በግንቦት ሀያ በአል ሰሞን የደርግን መውደቅና በደርግ መቃብር ላይ አዲሲቷ ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ እንደተገነባች ኢህአዴግ ሳይታክት ይነግረናል፡፡ የዲሞክራሲ መብቱ ኢህአዴግ እንደሚያወራው በተግባርም ይረጋገጥልኝ የሚል ነው፡፡ እንደአለመታደል ሆኖ ኢህአዴግ ግን አልገባውም፡፡በዘንድሮ የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች በዓል ላይም ኢህአዴግ የተጨበጨበለት ዲሞክራሲያዊ ህገመንግስት ማጽደቁንና ከደርግ በበለጠ ለህዝቦች እኩልነትና መብት እውቅና መስጠቱን ሊያስረዳን በእጅጉ ሞክሯል፡፡ ሆኖም እኛ ይህን በሚገባ እናውቃለን፡፡  የእኛ ጥያቄ ተግባራዊ አፈፃፀሙ ላይ ነው፡፡ ይሄን ግን ፈጽሞ የተረዳ አይመስልም - ኢህአዴግ፡፡አሁን ኢህአዴግ የዛሬ ሃያ አመት ጥየዋለሁ ከሚለው ከደርግ ጣዕረሞት ጋር የምናብ ትንቅንቁን እርግፍ አድርጐ ትቶ ራሱን ከሌሎች ዲሞክራሲያዊ ሀገራት ጋር ማወዳደር መጀመር አለበት፡፡በዲሞክራሲ ግንባታ በኢኮኖሚና በማህበራዊ ኑሮ የረጅም ዘመን ልምድ ካላቸው የአሜሪካና የአውሮፓ ሀገራት ጋር ኢህአዴግ ራሱን እንዲያወዳድር ባናጨናንቀው እንኳ (አቻው ስላልሆኑ) ቢያንስ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ ውጤት ካስመዘገቡት እንደ ጋና፣ ሞሪሽየስና የመሳሰሉት የአፍሪካ ሀገራት ጋር ራሱን በማወዳደር ያሉበትን በርካታ ጉድለቶች እንዲሞላ እንመኛለን፡፡ዲሞክራሲያዊ ህገመንግስት ማጽደቅና ለህዝቦች መብትና እኩልነት እውቅና መስጠት ብቻውን አንድን ሀገርና መንግስት ከሌላው የተሻለ ዲሞክራሲያዊ መንግስት ነው እንደማያስብለው ለማናችንም ቢሆን ግልጽ ነው፡፡ ዋናው ቁምነገሩ ያለው በተግባር መተርጐሙ ላይ ነው፡፡ የኢህአዴግ በርካታ ጉድለቶች ያሉት ደግሞ ተግባር ላይ ነው፡፡ (እሱ ራሱ ችግሬ አፈፃፀም ላይ ነው እንደሚለው) ስለዚህ የፕሮፓጋንዳው ቀረርቶና ያለአቻው ፉክክሩ  ቀርቶ የሚያወራውን በተግባር እንዲያሳየን በአክብሮት እናሳስበዋለን፡፡ ያለአቻ ፉክክር ትዝብት ላይ ከመጣል በቀር የትም እንደማያደርስ ማወቅ ብልህነት ነው፡፡

 

 

Read 3443 times Last modified on Saturday, 17 December 2011 09:16