በኢትዮጵያና በአውስትራሊያ የተቀረፀው “ሴት” የደራሲና አዘጋጅ አወል ሃይረዲን ፊልም ዛሬ አዲስ አበባ በሚገኙ ሲኒማ ቤቶች ይመረቃል፡፡ ለዝግጅት ከሦስት ዓመት በላይ የፈጀው ፊልም፤ አሁን በሕይወት የሌሉት አርቲስት ምኒሊከ ወስናቸው እና አርቲስት በላይነሽ አመዴን ጨምሮ አብራር አብዶ፣ ዶር. ሶንግ፣ ጀማል አህመድና ሌሎችም ተውነውበታል፡፡ “ሴት” ለአወል የመጀመርያ ፊልሙ ነው፡፡ በመቅዲ ፕሮዳክሽን የተዘጋጀውና ናኦድ ጋሻው ፅፎ ያዘጋጀው “ዘራፍ” የቤተሰብ ኮሜዲ ፊልም ዛሬ በ8፣ 10 እና 12 ሰዓት በአዲስ አበባ በሚገኙ የግል ሲኒማ ቤቶችና በክልል ሲኒማ ቤቶች ይመረቃል፡፡ በዘጠና ደቂቃ ፊልሙ ላይ ሸዋፈራሁ ደስአለኝ፣ መለሰ ወልዱ፣ መቅደስ ፀጋዬ እና ሌሎችም በትወና ተሳትፈዋል፡፡