Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 10 December 2011 10:08

የአንጀሊና ፊልም ክስና ትችት በዛበት

Written by 
Rate this item
(0 votes)

የሆሊውዷ ኮከብ ተዋናይ አንጀሊና ጆሊ ለመጀመሪያ ጊዜ በዲያሬክተርነት የሰራችበት “ኢን ዘ ላንድ ኦፍ ብለድ ኤንድ ሃኒ” ፊልሟ ባለፈው ሰኞ የተመረቀ ሲሆን ገና ካሁኑ ክስና ትችት እያስተናገደ ነው፡፡
አንድ የክሮሺያ ጋዜጠኛ የፊልሙ ታሪክ ከ4 ዓመት በፊት ፅፌ ካሳተምኩት የቦስኒያን ታሪክ የሚተርክ መፅሃፍ የተወሰደ ነው ሲል አንጀሊና ጆሊን እንደከሰሰ ዘጋርዲያን ዘግቧል፡፡ አንጀሊና በበኩላ ፊልሙን ከመስራቷ በፊት ብዙ መፃህፍትን እንዳነበበችና ዶክመንታሪ ፊልሞችን እንዳየች ጠቅሳ የጋዜጠኛውን መፅሃፍ ግን አላነበብኩም ስትል ውንጀላውን አስተባብላለች፡፡ የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ድርጅት የበጎ ፍቃድ አምባሳደር የሆነችው አንጀሊና አዲሱ ፊልሟን ባስመረቀችበት ወቅት ከቦስኒያ የጉዲፈቻ ልጅ ታሳድግ እንደሆነ ተጠይቃ አስብበታለሁ ብላለች፡፡ የአንጀሊና አዲስ ፊልም ከቦስኒያውያንም ትችት ተሰዝንሮበታል - የፊልሙ ታሪክ በሰርቢያ ወታደር የወሲብ ጥቃት ስለደረሰባት ቦሲኒያዊት ሴት በአግባቡ አይገልፅም የሚል፡፡በአንድ የሰርቢያ ወታደርና ሙስሊም ቦስኒያዊት ሴት መካከል ያለውን ውስብስብ የፍቅር ህይወት የሚዳስሰው ፊልሙ፤ ከሁለት ሳምንት በኋላ በመላው አለም ይታያል፡፡ የ36 አመቷ አንጀሊና ጆሊ፤ በፊልም ተዋናይነት በአመት እስከ 30 ሚሊዮን ዶላር ከሚከፈላቸው ጥቂት የሆሊውድ ተዋናዮች አንዷ ናት፡፡

Read 2828 times