Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Print this page
Saturday, 10 December 2011 10:08

የቶክሾው ንጉስ ላሪ ኪንግ ሞትን እፈራለሁ አለ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

የ78 አመቱ የቶክ ሾው ንጉስ ላሪ ኪንግ ስሞት ሬሳዬ በማቀዝቀዣ ውስጥ ይደረግልኝ ሲል ተናገረ፡፡ ምክንያቱን አሟሟቴ ታውቆ ከሞት ሊመልሱኝ ከተቻለ ነው ሲል መናገሩ ታውቋል፡፡ በእርጅና ዘመኔ ሌት ተቀን የምፈራው ሞትን ነው ያለው ላሪ ኪንግ፤ ከሞትኩ በኋላ የት እንደምሄድ እርግጠኛ አይደለሁም ብሏል፡፡ ላሪ ኪንግ ስለሞት ያወራው በስሙ በተዘጋጀ የሲኤንኤን ልዩ እራት ግብዣ ላይ ነው፡፡ ኮናን ኦብራያን፤ ሻክ ኦኒል፤ ታይራ ባንክስ ከታዳሚዎቹ መካከል ይገኙበታል፡፡ ክራዮ ጄኒክስ በተሰኘ ህክምና ሬሳን በማቀዝቀዝ ሟችን ከሞት ለመመለስ በሚደረገው ጥረት የላሪ ኪንግ ተሳትፎ ትልቅ ማስታወቂያ ነው ተብሏል፡፡ በሚቺጋን የሚገኝ ኢንስቲትዩት ለተመሳሳይ ህክምና ማቀዝቀዣ ውስጥ የገቡ 107 ሰዎችን እንዳከማቸ የገለፀው ሎስ አንጀለስ ታይምስ፤ ከላሪ ኪንግ በፊት በአሜሪካን አይዶል ዳኝነቱ የሚታወቀው ሲሞን ኮዌልና ፓሪስ ሂልተንም ከሞታቸው በኋላ ተመሳሳይ ህክምና እንዲደረግላቸው መናዘዛቸውን አውስቷል፡፡ በአሜሪካ የብሮድካስቲንግ ኢንዱስትሪ ለ53 አመታት ያገለገለው ላሪ ኪንግ፤ ከ60ሺ በላይ ቃለ-መጠይቆችን በማድረግ በጊነስ የሪኮርድ መዝገብ ውስጥ ስሙ ሰፍሯል፡፡በሲኤንኤን ለ25 ዓመታት በየምሽቱ ሲያቀርብ የነበረውን ቶክ ሾው ካለፈው አንድ አመት ወዲህ ፒርስ ሞርጋን ተክቶት እየሰራ ይገኛል፡፡

Read 2610 times

Latest from