Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 10 December 2011 10:02

ቴይለር ስዊፍትና ኒኪ ማናጅ የቢልቦርድን ክብር ወሰዱ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

በሙዚቃው ኢንዱስትሪ የአመቱ ምርጥ ሴት አርቲስቶችን በማክበር የሚሸልመው ቢልቦርድ ዘንድሮ ለሰባተኛ ግዜ ባዘጋጀው የሽልማት ስነስርአት ቴይለር ስዊፍትና ኒኪ ማናጅን የአመቱ ኮከብ ዘፋኝና የአመቱ አዲስ ኮከብ መሆናቸውን አስታወቀ፡፡
“ስፒክ ናው” በተባለው አልበሟ በአለም ዙርያ 20 ሚሊዮን ቅጂ ሽያጭ ያገኘችው ቴይለር ስዊፍት፤ ሰሞኑን 22ኛ አመቷን የያዘች ሲሆን በግራሚ በአንድም ዘርፍ ሳትመለመል ብትቀርም በቢልቦርድ መፅሄት ተስተካካይ ክብር ተጎናፅፋለች፡፡
ቴይለር ስዊፍት ለሂፕ ሆፕ አርቲስቷ ኒኪ ማናጅ አድናቆት እንዳላት ለኤምቲቪ ኒውስ ስትገልፅ አብራት ለመስራት እንደምትፈልግም ተናግራለች፡፡ የትሪንዳድና ቶቤጎ ደም ያላት የ28 አመቷ ኒኪ ማናጅ፤ በቢልቦርድ የአመቱ አዲስ ኮከብ አርቲስት ተብላ መመረጧን በደስታ የተቀበለች ሲሆን በ54ኛው ግራሚ ለአመቱ ምርጥ የራፕ ብቃትና ምርጥ የራፕ አልበም ዘርፎች ታጭታለች፡፡ የኒኪ ማናጅ አልበም “ ፒንክ ፍራይዴይ” ዘንድሮ በአሜሪካ ብቻ 1 ሚሊዮን 670 ሺህ ቅጂ ተቸብችቦ ከክሪስ ብራውንና ከሪሃና አልበሞች የተሻለ ገበያ እንዳገኘ ቢልቦርድ አመልክቷል፡፡

Read 2163 times