Print this page
Saturday, 10 December 2011 09:33

“ኤችአይቪ - በቫይረሱ መያዝ፣ መገለል፣ መሞት... ዜሮ”

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(0 votes)

በአለም አዲስ በኤችአይቪ ቫይረስ ከሚያዙ ሰባት ሰዎች አንዱ ቫይረሱ ከእናት ወደልጅ በመተላለፍ ነው፡፡ 
በአለም ከኤችአይቪ ቫይረስ ጋር ከሚኖሩ እናቶች 114,000 ሕጻናት ከቫይረሱ ነጻ ሆነው የመወለድ እድል ገጥሞአቸዋል፡፡
(centers for disease control and prevention (CDC)
ህዳር 21 (December 1st ) የአለም ኤይድስ ቀን በአለም አቀፉ ህብረተሰብ ከኤችአይቪ ጋር በተያያዙ የተለያዩ ሁነቶች ላይ በጋራ መግባባት መንፈስ ውይይት የሚንሄድበት በተለያየ መንገድ ታስቦ የሚውል ቀን ነው፡፡

ይህ ቀን በቫይረሱ ምክንያት ለህልፈት የተዳረጉት የሚታሰቡበት ፣ከቫይረሱ ጋር የሚኖሩ ድጋፍና አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችለው ሁሉ የሚመከርበት፣ ከኤችአይቪ ነጻ የሆነ ትውልድ እንዲገኝ አስፈላጊው እርምጃ እንዲወሰድ ባለሙያዎች የሚመክሩበት ነው፡፡
በአለም ኤችአይቪ የሚባል ሕመም መኖሩ ሪፖርት የተደረገው እንደ አውሮፓ አቆጣጠር June 5/1981 ሲሆን በኢትዮጵያ ሪፖርት የተደረገው በሶስት አመት የጊዜ ልዩነት በ1984 እኤአ ሪፖርት ተደርጎአል፡፡
የአለም ኤይድስ ቀንን መሰረት በማድረግ ከJune 4-8/ ICASA ማለትም በኤችአይቪ ኤይድስ ላይ የሚያተኩረው የአፍሪካ ሀገራት ስብሰባ 16ኛውን በኢትዮጵያ አካሂዶአል፡፡
አለም አቀፉ የኤይድስ ቀን የአመቱ መሪ ቃል: Zero New HIV Infections. Zero Discrimination and Zero AIDS-Related Deaths. ማለትም አዲስ በቫይረሱ የሚያዙ ፣በቫይረሱ ምክንያት የሚደርሰው መድሎና መገለል እንዲሁም ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ የሚከሰቱ ሞቶች ዜሮ እንዲሆኑ የሚል ሲሆን ይህ መሪ ቃል በ2012/ እኤአ የሚወሰን ሳይሆን እስከ 2015/እኤአ ድረስ የሚያገለግል ነው፡፡
የዘንድሮውን አለም አቀፍ የኤይድስ ቀን ምክንያት በማድረግ ዩ ኤን ኤይድስ እስከ 2010 /እኤአ መጨረሻ ድረስ ያለውን የአለም አቀፍ የኤችአይቪ ገጽታ ይፋ አድርጎአል፡፡ በዚህ መረጃም መሰረት፡-
በአለም አቀፍ ደረጃ ከኤችአይቪ ቫይረስ ጋር የሚኖሩ ሰዎች ወደ ሰላሳ አራራት 34/ ሚሊዮን ሰዎች ይደርሳሉ፡፡
በ2010 አዲስ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 2.67 ሚሊየን ይሆናሉ፡፡
በ2010 በአለም ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ ለህልፈት የተዳረጉት 1.76 ሚሊዮን ሰዎች ናቸው፡፡
( UNAIDS 2011 World AIDS Day report)
ሕጻናት እና እናቶች ፡-
በ2010 በአለም አቀፍ ደረጃ ወደ 390.000/ የሚሆኑ ህጻናት ከቫይረሱ ጋር ከሚኖሩ እናቶች ሲወለዱ በቫይረሱ የተያዙ ሆነዋል፡፡
በእርግጥ ህጻናቱን በሚመለከት በተለይም ከ15 አመት በላይ የሆኑት ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ ያለው የሞት መጠን ቀንሶ ታይቶአል፡፡ የዚህም ምክንያት ለእርጉዝ እናቶችና ለህጻናቱ ፀረ ኤችአይቪና ፐሮፒላክሲስ የተሰኘው መድሀኒት በመሰጠት ላይ ስለሆነ መሆኑን መረጃው ይጠቅሳል፡፡ በአሁኑ ወቅት በአለም ላይ በዝቅተኛና በመካከለኛ ደረጃ ኑሮአቸውን በሚገፉ አገሮች ወደ 6.6 ሚሊየን የሚሆን ሰዎች ፀረ ኤችአይቪ መድሀኒት በመውሰድ ላይ መሆናቸውንም የዩኤን ኤይድስ መረጃ አረጋግጦአል፡፡
እስከ 2015/ እኤአ ድረስ የተሰየመው አለም አቀፍ መሪ ቃል የምእተ አመቱን የልማት ግብ ከማሳካት አንጻር ለተግባራዊነቱ ከፍተኛ እንቅስቃሴን የሚጠይቅ ነው፡፡ በዚህም መሰረት እስከ 2015 /እኤአ /ኤችአይቪን በሚመለከት -፡
ልቅ በሆነ የግብረስጋ ግንኙነት አማካኝነት የሚተላለፈው የኤችአይቪ ቫይረስ በተለይም ወጣቶችን እንዲሁም ወንድ ለወንድ ወሲብ የሚፈጽሙትን በከፍተኛ ደረጃ የሚጎዳ እንደመሆኑ በአጠቃላይ ጉዳቱ አሁን ካለበት በግማሽ ያህል እንዲቀንስ፣
ኤችአይቪ በአሁኑ ወቅት ከእናት ወደልጅ የሚኖረውን መተላለፍ እና በእናቶች ላይ የሚያደርሰውን ሞት አሁን ካለበት በግማሽ ያህል ዝቅ እንዲል፣
አዲስ በቫይረሱ የሚያዙ ሁሉ ራራሳቸውን በመድሀኒት እንዲንከባከቡ ማስቻል፣
ፀረ ኤችአይቪ መድሀኒት በቫይረሱ ለተያዙ ሁሉ ማዳረስ፣
ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ በሳንባ በሽታ ምክንያት የሚደርሰውን ሞት አሁን ካለበት በግማሽ መቀነስ፣
ከቫይረሱ ጋር ለሚኖሩ ሰዎች አስፈላጊው እንክብንቤ እና ድጋፍ እንዲደረግላቸው ማስቻል፣
ለሴቶች እና ለልጃገረዶች በተለያም በቫይረሱ ለተያዙት ከጠቅላላው በኤችአይቪ ምክንያት ከሚሰጠው አገልግሎት ግማሽ ያህሉን እንዲያገኙ ማስቻል፣
በተለይም ከጾታ ጋር በተያያዘ የሚፈጠረውን ጥቃት እና ሌሎችንም መሰል ሁኔታዎች አሁን ካለበት ዝቅ ማድረግ ከምእተ አመቱ የልማት ግቦች መካከል ሲሆኑ የአለም የኤይድስ ቀን እስከ 20015 ድረስ ትኩረት የሚያደርግባቸው ናቸው እንደ መረጃው፡፡
ICASA 16ኛውን በኤችአይቪ ላይ ያተኮረ ስብሰባውን ሲያካሂድ የቀጣዩ አመት መሪ ቃል Own, Scale-up and Sustain በሚል ነው፡፡
Own :-
ኤችአይቪን የራራስ ጉዳይ አድርጎ መግታት በሚቻልበት መንገድ ሁሉ መንቀሳቀስ፣
የኤችአይቪን ስርጭት ፣ከቫይረሱም ጋር በተያያዘ የሚከሰተውን ሞት እንዲሁም አድሎና መገለልን ለማስወገድ እንዲቻል ለራራስ ቃል መግባት እና አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረግ፣
በጉዳዩ ላይ የሚመለከታቸው የአፍሪካ መሪዎች አጋር ድርጅቶችና ህብረተሰቡን ማንቃት፣ በጉዳዩ ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ ማስቻል የመሳሰለውን የሚመለከት ሲሆን ዋናው ነገር ችግሩን ለመቅረፍ በባለቤትነት መቆም ነው፡፡
Scale-up and Sustain :-
በኤችአይቪ ኤይድስ ዙሪያ እውቀትን እና ችሎታን መጋራትን፣ አገልግሎት ማበርከትን ፣ጥሩ ጥሩ ልምዶችን በአፍሪካና በአለም አቀፍ ደረጃ መለዋወጥን ከኤ ችአይቪና ከግብረ ስጋ ግንኙነት ጋር በተያያዘ የሚተላለፉ በሽታዎችን በሚመለከት ጥራትንና ደረጃቸውን የጠበቁ መረጃዎችን መካፈልን ...ወዘተ ደረጃውን በማሳደግና ቀጣይነት ባለው መንገድ መተግበር መቻልን የሚያመለክት ነው፡፡
ከላይ የተገለጸውን ለመፈጸም ተዋናዮች እና ይመለከታቸዋል የተባሉት የተለዩ ሰዎች ሳይሆኑ ሁሉም ማለትም ፖለቲከኞች ሳይንቲስቶች ህብረተሰቡ የግልና የመንግስት ተቋማት ሁሉ እጅ ለእጅ ተያይዘው ሊሰሩበት የሚገባ መሆኑን ነው የአፍሪካው መሪ ቃል የሚያመለክተው፡፡
በአጠቃላይም ኤችአይቪን እና በግብረስጋ ግንኙነት አማካኝነት የሚተላለፉ በሽታዎችን ለመከላከል አስፈላጊውን አገልግሎት ፣ጥንቃቄና ድጋፍ ፣በፖሊሲ እና እቅድ የተዘረጋ አሰራርን የሚፈልግ በመሆኑ የሚመለከተው ሁሉ በግንባር ቀደምትነት ሊወጣው የሚገባው መሆኑን የአፍሪካው ስብሰባ አስምሮበታል፡፡
ኤችአይቪ ኤይድስን ስርጭቱን ለመግታትና ብሎም ጉዳቱን ለመቀነስ እንቅስቃሴው በየትኛውም መንገድ እክል እንዳይገጥመው፣ እንዲሁም የፋይናንስና የኢኮኖሚ አቅሙ እንዳይዳከም ፣እስከአሁን ይታይ የነበረው ኤች አይቪን ለመከላከል የሚኖረው ድጋፍ መዋዠቅ ወደፊት እንዳይኖር ትኩረት ያሻዋል፡ ይህም ቀጣይነት ባለው እና በተሸሻለ ሁኔታ ችግሩን ለመቅረፍ እንደሚረዳ የታመነበት ነው፡፡
እንደ ዩ ኤን ኤይድስ ሪፖርት ከሰሃራ በታች ባሉት አገሮች በ2010/እኤአ፡-
ከቫይረሱ ጋር የሚኖሩ 22.9 ሚሊዮን ሰዎች ናቸው ፡፡
አዲስ በቫይረሱ የሚያዙ 1.9 ሚሊዮን ይደርሳሉ፡፡
ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ የሚሞቱ 1.2 ሚሊዮን ሰዎች ናቸው ፡፡ የተለያዩ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በአለም አቀፍ ደረጃ በ2010 ከተመዘገበው ከቫይረሱ ጋር ከሚኖሩ ከ34/ሰላሳ አራራት ሚሊዮን ከቫይረሱ ጋር ከሚኖሩ ሰዎች መካከል 2/3ኛው የሚገኙት ባልለሙት አገሮች ነው፡፡ እንዲሁም በ2010 አዲስ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች በሚል ከተመዘገበው 2.67 ሚሊዮን ሰዎች 3/4ኛው የሚገኙት ባላደጉ አገሮች ነው፡፡
በኢትዮጵያ በ2010 እኤአ/ በአማካይ 1.2 ሚሊዮን ያህል ሰዎች ከቫይረሱ ጋር እንደሚኖሩ ተረጋግጦአል፡፡

 

Read 3545 times Last modified on Saturday, 10 December 2011 09:50