Sunday, 19 January 2014 00:00

የድንጋይ ዋጋ በእጥፍ ጨመረ

Written by  ማህሌት ፋሲል
Rate this item
(1 Vote)

ለኮንስትራክሽን ግብአት የሚውለው ድንጋይ ዋጋ በእጥፍ መጨመሩን በተለያዩ የኮንስትራክሽን ስራ የተሰማሩ መሀንዲሶችና ባለሀብቶች ገለፁ፡፡ በፊት በ2 እና 3 ብር ይገዛ የነበረው ድንጋይ፤ በአሁኑ ሰአት በእጥፍ ጨምሮ 5 እና 6 ብር ገብቷል ብለዋል። በተለያዩ የኮንስትራክሽን ሳይቶች ተዟዙረን ያነጋገርናቸው መሀንዲሶችና ባለሀብቶች እንደገለፁት፣ ዋጋው ከጥቂት ቀናት በፊት እንደጨመረ ጠቁመው፤ ለየትኛው አካል አቤት ማለት እንዳለባቸው አለማወቃቸውን ለአዲስ አድማስ ገልፀዋል፡፡ በመንግስት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶትና እንደ አንድ የስራ ፈጠራ ተቆጥሮ የነበረው የኮብልስቶን መንገድ ስራም በድንጋይ እጥረት ምክንያት እየተስተጓጐለ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡

Read 2646 times