Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 03 December 2011 08:41

ዲኬቲ በጥበብ የታገዘ የአንድ ወር ዘመቻ ጀመረ ለአረጋውያን ትኩረት እንዲሰጥ ተጠየቀ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

የዘንድሮውን የኤድስ ቀን ምክንያት በማድረግ ዲኬቲ ኢትዮጵያ ከአጋሮቹ ጋር በመሆን ለአንድ ወር የሚቆይ ዘመቻ ጀመረ፡፡ “አንድም ሰው በኤችአይቪ እንዳይያዝ ሃላፊነታችንን እንወጣ” በሚል መሪ ቃል ባሳለፍነው ሳምንት በተጀመረውና የሁለተኛ ደረጃ እና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችን በሚያካትተው ዘመቻ፤ ሕብረተሰቡ በተለይም ወጣቶችና ሌሎች ተጋላጮች ስለ ጤናማ ወሲብ፣ የኮንዶም አጠቃቀምና ስለኤችአይቪ ኤድስ ግንዛቤ ያገኛሉ፡፡ 24 ሰአት የሚሰሩ የኮንዶም መሸጫ ሱቆችም ይከፈታሉ፡፡ የካርቱን ሥራ፣ የዘፈን፣ የፊልም፣ የ“ወሲብ ተዳዳሪዎች” የታለንት ሾው እና ሌሎች ዝግጅቶች በአዲስ አበባና በክልል ዋና ዋና ከተሞች እንደሚቀርቡ ዲኬቲ አስታውቋል፡፡

ይህ በዚህ እንዳለ ሔልፕ ኤጅ ኢንተርናሽናል በኤች አይቪ ኤድስ በሚሞቱ ሰዎች ምክንያት ያለ ልጅ በመቅረት የልጅ ልጅ የሚያሳድጉ አረጋውያን ትኩረት ተነፍጓቸዋል አለ፡፡ በአረጋውያን ዙርያ የሚሰራው ሄልፕ ኤጅ ኢንተርናሽናል ገለፃ መሠረት ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገሮች 1.6 ሚሊየን አረጋውያን 12 ሚሊየን በኤች አይ ቪ አንድ ወይ ሁለቱንም ወላጆቻቸውን ላጡ ወላጅ የሌላቸው ልጆች ይንከባከባሉ፡፡ በዚሁ ምክንያት ከጡረታ መውጫ ጊዜአቸው በኋላም ቤተሰቦቻቸውን ለመደጎም ይሰራሉ ለዚህም ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል ብሏል ድርጅቱd በመግለጫው፡፡

 

Read 2281 times Last modified on Saturday, 03 December 2011 08:43