Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Print this page
Saturday, 03 December 2011 08:37

ጄኒፈር አኒስተን ልታገባ ነው

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ሳላገባ መኖር እችላለሁ ስትል የነበረችው ጄኒፈር አኒስተን ጀስቲን ቴሮክስ ከተባለው የቅርብ ግዜ ፍቅረኛዋ ጋር ጋብቻ ልትፈፅም መሆኑን ኦኬ የተባለው ማጋዚን ሰሞኑን ዘገበ፡ ጄኒፈር በምስጥራዊ ፕሮግራም በሜክሲኮ ካቦ ሳን ሉካስ ከተማ ይደረጋል የተባለው የጄኒፈር አኒስተን እና የጀስቲን ቴሮክስ ጋብቻ ቀለል ያለና ብዙም ወጭ እንደማይኖረው ዘገባው አመልክቷል፡፡የ42 አመቷ ጄኒፈር አኒስተንና የ39 አመቱ ጀስቲን ቴሮክስ በኒውዮርክ 6 ሚሊዮን ዶላር ዋጋ ባለው አፓርትመንት አብረው መኖር ከጀመሩ ወራት ተቆጥረዋል፡፡

ጄኒፈር አኒስተን ከብራድ ፒት ጋር ከ11 አመት በፊት በሆሊውድ ድንቅ ተብሎ የተወደሰ የመጀመሪያ ትዳሯን መመስረቷ ሲታወስ ይሄ ጋብቻዋ ከ5 አመታት በኋላ ፈርሷል፡፡ በአንድ ፊልም ስራ ከ8-10 ሚሊዮን ዶላር የሚከፈላት ጄኒፈር አኒስተን እስከ 110 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት ሃብት እንዳላት ይገለፃል፡፡ ዘንድሮ የተወነችባቸው “ጀስት ጎዊዝ ኢት” 215 ሚሊዮን ዶላር “ሆረብል ቦስስ” 211 ሚሊዮን ዶላር በአለም ዙርያ አስገብተዋል፡፡

Read 3274 times

Latest from