Saturday, 28 December 2013 10:40

ሜቄዶንያ ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ ገንዘብ አሰባሰበ

Written by  መንግሥቱ አበበ
Rate this item
(0 votes)

•    ሁለት መኪኖች በስጦታ አገኘ  
•    የተረጂዎችን ቁጥር ወደ አንድ ሺ ሊያሳድግ ነው  

መቄዶንያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከል፤ “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን በቂ ነው” በሚል መርህ

ባለፈው እሁድ በግሎባል ሆቴል ባካሄደው የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም፣ ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ አሰባሰበ፤ ሁለት

መኪኖችም በስጦታ አግኝቷል፡፡
በዕለቱ በተካሄደው የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም፣ በጥሬ ገንዘብ የተሰጠ 274ሺ ብር፣ ከሥዕል ጨረታ 705ሺ ብር፣

ከቲኬት ሽያጭና ከስፖንሰር 300ሺ ብር፣ ቃል የተገባ 1ሚሊዮን 739ሺ ብር በአጠቃላይ 3 ሚሊዮን አስራ ስምንት ሺ

ብርያገኘ ሲሆን በዓይነት ደግሞ ከበጐ አድራጐትና ማኅበራት ኤጀንሲ አንድ ዲ ኤክስ የቤት መኪና፣ ከአቢሲኒያ ዱቄት

ፋብሪካ አንድ ዳማስ መኪና ማግኘቱን አስታውቋል፡፡
ዳሽን ባንክ፤ ማዕከሉ ለሽያጭ ያቀረበውን ሥዕል 200ሺ ብር የገዛ ሲሆን የባንኩ የቦርድ ሊቀመንበር አቶ ተክሉ ኃይሌ

ደግሞ በግል ድርጅታቸው ስም የማዕከሉ ተረጂ የሆኑትን አረጋዊ ምስል በ300ሺ ብር ተጫርተው ገዝተዋል፡፡ አቢሲኒያ

ዱቄት ፋብሪካ ከመኪናው በተጨማሪ 120ሺ ብር ሰጥቷል፡፡
ቀቅ ኮንስትራክሽን ለጨረታ የቀረበ ሥዕል በ100ሺ ብር የገዛ ሲሆን ኒያላ ኢንሹራንስ የ100ሺ ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡

ጌታቸው አፅብሃ ሕንፃ ተቋራጭና SRIM.plc እያንዳንዳቸው 120ሺህ ብር የለገሱ ሲሆን፣ ቢጂአይና እንይ ሪል ስቴት

እያንዳንዳቸው 50ሺ ብር ሰጥተዋል፡፡ አምባሳደር ልብስ ስፌት ፋብሪካ በማዕከሉ ለሚገኙ 300 አረጋውያንና የአዕምሮ

ሕሙማን ሙሉ ልብስ ለማልበስ ቃል ገብቷል፡፡ በማዕከሉ በበጐ ፈቃደኝነት የሚያገለግሉት ዶ/ር ጌታቸው ተድላ፤

ካሳተሟቸው ሁለት መጻሕፍት 900 ኮፒና አንድ ሥዕል                      (በዋጋ ሲተመን 167,500ብር)

ሰጥተዋል፡፡ የገለፀው የማዕከሉ መሥራች አቶ ቢኒያም በለጠ፤ በዕለቱ የተሰበሰበው ገቢ ማዕከሉ በቀጣይ ዓመት

የተረጂዎችን ቁጥር አንድ ሺህ ለማድረስ ለሚያደርገው እንቅስቃሴ እንደሚውል ገልፃ፤ የገለፀው የማዕከሉ መሥራች አቶ

ቢኒያም በለጠ፤ ለማዕከሉ ድጋፍ ያደረጉትን በሙሉ በተረጂዎቹ ስም አመስግኗል

Read 2130 times