Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Print this page
Saturday, 03 December 2011 08:36

ማርቲን ስኮርሴሲ በዲጅታል ቴክኖሎጂ የተራቀቁ ፊልሞችን አወገዘ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ማርቲን ስኮርሴሲ ከቢቢሲ ጋር ባደረገው ቃለምልልስ በዲጅታል ቴክኖሎጂ የሚቀናበሩ ፊልሞች ገበያ ስለደራላቸው በመደበኛ የሲኒማ የቀረፃ ስልቶች የተሰሩ ፊልሞች የሚያሳዩትን የሙያ ብቃት ሊጋርዱ አይገባም ሲል ተናገረ፡፡ ስኮርሴሲ “ሁጎ” የተባለና በ1930ዎቹ በፈረንሳይ የባቡር መናሀርያ ጎዳን ተዳዳሪ በነበረ ወላጅ አልባ ህፃን ህይወት ላይ የተሰራ ፊልሙን ሰሞኑን አስመርቋል ቦክስ ኦፊስን በገቢ የነገሱበት ፊልሞች በአሰራራቸው በኮምፒውተር ቅንብር የታጀቡ ትእይንቶችን ማብዛታቸውና ታሪካዊ ስፍራዎችን በዲጂታል ቴክኖሎጂ በመቀመር የሚሰሩ ባለሙያዎች የሲኒማ ክብርን እያጎደፉ ናቸው ብሎ ሶኮርሴሊ አውግዟል ፡፡በቦክስ ኦፊስ አምስተኛ ደረጃን የያዘው አዲሱ የማርቲን ስኮርሴሲ ፊልም “ሁጎ” በ150 ሚሊዮን ዶላር በጀት የተሰራ ሲሆን ባለፈው ሳምንት ለእይታ ሲበቃ በሰሜን አሜሪካ ብቻ 11.4 ሚሊዮን ዶላር አስገብቷል፡፡

ከሮበርት ዲኔሮ ጋር ስምንት ከሊዮናርዶ ዲካርፒዮ ጋር አራት ፊልሞችን የሰራው ማርቲን ስኮርሴሲ ከ5 አመት በፊት “ ዘዲፓርትድ” በተባለው ፊልሙ የኦስካር ክብርን የተቀዳጀ ሲሆን በ48 አመታት የስራ ዘመኑ ዲያሬክት ያደረጋቸው ፊልሞች በአለም ዙርያ 854 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ሆኖባቸዋል፡፡ከማርቲን ስኮርሴሲ ፊልሞች “ጋንግስ ኦፍ ኒውዮርክ”፤ ካሲኖ፤ ዘ አቪዬተር ይጠቀሳሉ፡፡ ሰሞኑን ስኮርሴሲ ከ60 አመታት በፊት በብሮድዌይ የታዩ ታላላቅ ቴያትሮችን ወደ ፊልም በመቀየር ስራው እንደሚያተኩር ሲገልፅ የፍራንክ ሲናትራ ህይወትን የሚተርክ ፊልሙን ሊዮናርዶ ዲካርፒዮ እንዲተውንለት መፈለጉን አስታውቆ ጣልያናዊ የዘር ግንድ ካላቸው አንጋፋ ተዋናዩች ሮበርት ዲኔሮ፤አልፓቺኖና ጆ ፔስኪ ጋር “ ዘአይሪሽ ማን” በተባለ የፊልም ስራ ፕሮጀክቱን መጀመሩንም ተናግሯል፡፡

 

Read 3491 times Last modified on Saturday, 03 December 2011 08:37

Latest from