Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Print this page
Saturday, 03 December 2011 08:22

“ጤነኛ እናት... ጤነኛ ጨቅላ...”

Written by 
Rate this item
(0 votes)

በታዳጊ አገሮች በአሁኑ ጊዜ የህጻናትና እናቶች ሞት የመቀነስ ሁኔታ እያሳየ ቢሆንም ከሚመዘገቡት የህጻናት የሞት ቁጥሮች 40 ያህሉ ከአምስት አመት በታች ያሉ ሕጻናት ናቸው፡ ከምእተ አመቱ የልማት ግቦች መካከል የእናቶችንና የህጻናቱን ሞት መቀነስ ትኩረት የተሰጠው ሲሆን ይህንንም ለማሳካት አገሮች ያላሰለሰ ጥረት በማድረግ ላይ ናቸው ፡፡ የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር የእናቶችን ሞት በመቀነሱ ረገድ በአገራችን የተተለመውን እቅድ ለማገዝ የበኩሉን ጥረት እያደረገ ሲሆን ህዳር 7/2004 የእናቶችና የሚወለዱ ሕጻናትን ጤንነት መረጃ አሰባሰብን በሚመለከት በጋራ አብሮአቸው ከሚሰራባቸው የጤና ተቋማት ተወካዮች ጋር የአንድ ቀን ስብሰባ አድርጎ ነበር፡፡ በስብሰባው ላይ ቀርበው ከነበሩ ምስክርነቶች መካከል አንዱን ለንባብ ብለነዋል፡፡

“አንዲት እናት እርግዝናዋ ሰባት ወር ሲደርስ ደም ይፈሳታል፡፡ ይህች ሴት ኑሮዋ ወደ መቂ አካባቢ ሲሆን ያገባች እና እርግዝናዋም የመጀመሪያ ነው፡፡ በድንገት ስትታመም ቤተሰቦቿ ካለችበት የመኖሪያ አካባቢ የሶስት ሰአት መንገድ ተሸክመው መቂ ወደሚገኘው ክሊኒክ ነበር የወሰዱአት፡፡ በዚያም ልትረዳ ስላልቻለች ሞጆን አቋርጠው ወደ ደብረዘይት ሆስፒታል ያመጡአታል፡፡ ደብረዘይት ስትመጣ የእርግዝና ክትትል ያልነበራትና ምንም የሕክምና ምርመራ ያላደረገች ከመሆኑዋም በላይ ደም ያለማቋረጥ ይፈሳት ነበር፡፡ ብዙ ሰአት የተጉዋዘችው ይህች እናት ከሌሊቱ ዘጠኝ ሰአት እንደደረሰች የደም ግፊቷ ሲለካ 80/50 የሆነ እና የጤናዋ ሁኔታ አስቸጋሪ ደረጃ ላይ የደረሰች ነበረች፡፡ይህች ሴት በደብረዘይት ሆስፒታል ስትደርስ በሆስፒታሉ የነበረው ችግር የደም አለመኖር ነበር፡፡ ነገር ግን እንደምንም በመሯሯጥ አንድ ዩኒት ደም በመገኘቱ ኦፕራሲዮን ተደርጋ ሕይወቷን ለማትረፍ ተችሎአል፡፡ ይህች ሴት መሟላት የሚገባቸው ነገሮች ባለመሟላታቸው ሆስፒታልም ከደረሰች በሁዋላ ከሌሊቱ ዘጠኝ ሰአት እስከቀኑ ሰባት ሰአት ድረስ አገልግሎት አላገኘችም ነበር፡፡ የእናቶችንና የሚወለዱ ሕጻናትን ጤንነት በሚመለከት ከዚህ መገንዘብ የሚቻለው ...
እንኩዋንስ በጣም በእርቀት አካባቢ ኑሮአቸውን የመሰረቱ ቀርተው እንደዚህች እናት ለከተሞች ቅርብ በሚባል አካባቢም ያሉት ቢሆኑ ምን ያህል የጤና አገልግቱን በአቅራቢያቸው ማግኘት ይችላሉ?
እናቶች የጤና ተቋማቱን በአቅራራቢያቸው ካለማግኘታቸው የተነሳ የእርግዝና ክትትል ስለማያደርጉ በእርግዝናውና በመውለድ አጋጣሚው የሚከሰተው ችግር እንዳለ ሆኖ ተያይዞ ለሚመጣው ለማንኛውም የጤና ችግር የተጋለጡ ይሆናሉ፡፡
የጤና አገልግሎቱ ወደሚገኝበት አካባቢ ለማድረስ በሚደረገው ጥረትም የመጉዋጉዋዣው እጥረትና የመንገድ አለመኖር ተዳምሮ እናቶች በምጥ ሰአት አደጋ ላይ ይወድቃሉ፡፡
እናቶቹ ረዥም መንገድ ተጉዘው፣ ተንገላትተው ከጤና ተቋማቱ ቢደር ሱም በአንዳንድ አካባቢ በተለይም ለኦፕራራሲዮን የሚያስፈልጉት ነገሮች ተሟልተው አለመገኘታቸው ሌላው ሊታይ የሚገባው ችግር ነው ፡በደብረዘይት ሆስፒታል ኦፕራራሲዮን ለሚደረግ ሰው የሚሰጥ ደም አልነበረም ..
ምስክርነት ...ዶ/ር አስፋው ፈከንሳ ከደብረዘይት ሆስፒታል
የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር ኢሶግ የእናቶችና ሕጻናትን ሞት በመቀነሱ ረገድ የሚሰሩ ስራራዎችን መረጃ በትክክል የማሰባሰብ ሰራራ በሚመለከት ማብራራሪያ የሰጡን ዶ/ር ይርጉ ገ/ሕይወት ረዳት ፕሮፌሰር በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሕክምና ፋክልቲ መምህርና የማህጸንና ጽንስ ሕክምና እስፔሻሊስት አንዲሁም የኢሶግ ፕሬዝዳንት ናቸው፡፡
ዶ/ር ይርጉ እንደገለጹት LOGIC በሚባለው ፕሮጀክት ማለትም (Leadership in obstetrics &gynecology for impact change) ዘጠኝ ሆስፒታሎችና አርባ አምስት ጤና ጣቢያዎች ውስጥ የሚሰሩ ጤና ሙያተኞችን ለውጥ በሚያመጣና አገልግሎትን በሚያሻሽል መንገድ መረጃ ማሰባሰብና ማጠናከር እንዲሁም ለእቅድ የአገልግሎት ጥራታቸውን ምን እንደሚመስል ማየት እንዲችሉና እንዴት ማሻሻል እንዳለባቸው እውቀት ለማስጨበጥ የሚያስችል ስልጠና ህዳር 7/2004 ለአንድ ቀን ተሰጥቶአል፡፡ ይህም ቀደም ሲል የሞሉትን መረጃና የሰሩትን ስራ እርስ በእርሳቸው የሚነጋገሩበትና ልምድ የሚለዋወጡበት ነው፡፡
የሚሰራው ስራ የጤና አገልግሎቱን የማገዝ ስራ ነው፡፡ መረጃም የሚሰበ ሰብባቸው በጤናው ስራ ውስጥ የጤና መረጃ አሰራር በቋሚነት የሚሰራበት ሲሆን ሰራተኞቹ የሚያገኙዋቸውን መረጃዎች ሰብስቦ ማስተላለፍ ብቻ ሳይሆን በቅርበት ማየት እንዲችሉ የሚያስችል ነው፡የተገኘው መረጃ ለዚያው ጤና ድርጅት አገልግሎቱ ምን እንደሚመስል ለማየትና ያንኑ መረጃ ተጠቅሞ ያለውን ክፍተት በማወቅ መሻሻል የሚችልበትን መንገድ እንዲያዩ የሚያስችል ነው፡፡ መረጃው እየተሰበሰበ ወደ ክልል እና ወደ ማእከል የሚመጣ ሲሆን መሰረታዊው ነገር መረጃውን የሚያመነጨው የጤና ድርጅት ያንን መረጃ መሰብሰብና ማስተላለፍ ብቻ ሳይሆን ሁኔታውን በመመልከት የአገልግሎቱን ጥራት የሚለካበትና የሚሻሻል ነገር ካለ ማሻሻል እንዲያስችል የሚያደርግ ነው፡፡
ይህ ፕሮግራም የሚያተኩረው በእናቶችና በህጻናት ጤንነት ላይ ነው፡፡ የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር ዋና አላማው በኢትዮጵያ ውስጥ የእናቶች ጤንነት የሚሻሻልበትን ፣የእናቶች ሞት የሚቀንስበትን ጉዳዩ ከሚመለከታቸውና አግባብ ካላቸው አካላት ጋር አብሮ መስራት ከሚያደርጋቸው እንቅስቃሴ መካከል ሲሆን ይህንን እውቀት ለጤና ሙያተኞቹ መስጠት ያለውን የጤና ሂደት ይረዳል ተብሎ ይታመናል፡፡ ስለዚህ መረጃው ጥራት ስለሚኖረውና አገልግሎቱ ስለሚሻሻል ድምር ውጤቱ የእናቶችና አዲስ የተወለዱ ህጻናትን ጤንነት በመጠበቅና ሞትን በመቀነሱ ረገድ የተፈለገውን ግብ ለመምታት ያስችላል ብለዋል ዶ/ር ይርጉ ገ/ሕይወት ፡፡
ዶ/ር ይርጉ አክለው እንደገለጹትም የምእተ አመቱ የልማት ግቦች ውስጥ 5ኛው ተራ ቁጥር ከእናቶች ጤና ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ኢትዮጵያ በ2015 እንደ ኤሮፓ አቆጣጠር የእናቶችን ሞት በመቀነሱ ረገድ ቁጥሩን ወደ 271 የመቀነስ እቅድ ይዛለች፡፡ ባለፉት ጊዜያት ውስጥ በተደረጉት እንቅስቃሴዎች ለውጥ የተመዘገበ ሲሆን በአማካይ በየአመቱ የእናቶች ሞት ወደ 4.2 በመቶ እየቀነሰ ይገኛል፡፡ ነገር ግን የምእተ አመቱን የልማት ግብ ለማሳካት የእናቶች ሞት የሚቀንስበትን ይህንን ቁጥር በፍጥነት በመጨመር ወደ 5.5 ማድረስ ይጠበቅብናል፡ይህ ሲደረግ የተቀመጠውን ግብ መምታት ይቻላል፡፡
በስልጠናው እንደተካተተው በብዛት መረጃዎችን የሚወጡት በሁለት አይነት መንገድ ነው፡፡
በወሊድና በእርግዝና ምክንያት የሞቱ እንዲሁም በወሊድና እና በእርግዝና አማካኝነት ከፍተኛ የሚባል ሕመም የደረሰባቸውና የተረፉ እናቶች ይህ በሌላው አለም ቀደም ሲል የተጀመረ ሲሆን በእኛ አገር ግን አሁን ስራራ ላይ ለማዋል በእንቅስቃሴ ላይ ነን፡፡ የጤና ልማት አቅጣጫ መርሀ ግብሩ ላይ አራራተኛው ተራራ ቁጥር ላይ የምንገኝ ሲሆን ይህ አሰራራር በዚያም ላይ የተካተተ ነው፡፡ ምንም እንኩዋን በዘጠኝ ሆስፒታሎችና በ45 የጤና ጣቢያዎች ላይ የሚጀመር ቢሆንም የትልቁ የጤና እቅድ አላማ አካል ስለሆነ ምን ያህል የሚለውን ለመገመት ባይቻልም የተወሰነ ለውጥ ለማምጣት ለሚደረገው ርብርብ የራራሱ የሆነ አስተዋጽኦ ይኖረዋል እንደ ዶ/ር ይርጉ ገ/ሕይወት ማብራራሪያ ፡፡
ዶ/ር በስተመጨረሻም ይህ መረጃን የመሰብሰብ ፣መረጃውን መተንተን እና ማጥናት፣ በመረጃው ላይ የተመሰረተ የውሳኔ ሀሳብና እርምጃ ማውጣት ፣የተሰጡት የውሳኔ ሀሳቦች ከምን እንደደረሱ ማየት የሚገባ ሲሆን ይህንን ሁሉ ካለፈ በሁዋላ ሁለት መሰረታዊ ነገሮች እንዲደረጉ ይጠበቃል፡፡
የጤና ተቋሙ እራራሱ በጎ ለውጥ ለማምጣት መስራራት አለበት፡፡ ዳታ መሰብሰብ ብቻ ሳይሆን ወደሁዋላ ተመልሶ አገልግሎቱን ማሻሻል ይጠበቅበታል፡፡
የሚገኙት ለውጦች ወይም መረጃዎች በማእከል ደረጃ የሚታዩበት አካሄድ የሚኖር ሲሆን የተወሰነው ደግሞ በዚያው መረጃው በተገኘበት የሚመለስበት አካሄድ ሊኖር ይችላል፡፡
በዚህ መንገድ ስራው ተያያዥነት ባለው አካሄድ ከተሰራ የእናቶችንና የሚወለዱ ሕጻናትን ጤንነት ለመጠበቅና ሞትን ለመቀነስ የሚረዳ አሰራር ስለሚሆን ጅምሩ ጠንክሮ ለውጤት እንዲበቃ ሁሉም የበኩሉን እንዲጥር ያስፈልጋል ብለዋል ዶ/ር ይርጉ ገ/ሕይወት ረዳት ፕሮፌሰር በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሕክምና ፋክልቲ መምህርና የማህጸንና ጽንስ ሕክምና እስፔሻሊስት አንዲሁም የኢሶግ ፕሬዝዳንት ፡፡

 

Read 3288 times Last modified on Saturday, 03 December 2011 08:24

Latest from