Print this page
Saturday, 30 November 2013 11:12

የድሬዳዋ የጉዞ ማስታወሻዬ!

Written by  ነቢይ መኰንን
Rate this item
(1 Vote)

ባለፈው እትም ከአቶ ብርሃነ የድሬዳዋ አክሽን የበጐ አድራጐት ማህበር ሰብሳቢ ጋር ውይይት ስንጀምር ነበር

ያቆምኩት፡፡ ከዛው እንቀጥል፡፡
“ምንድነው exactly (በትክክል) የምትፈልገው?” አሉኝ አቶ ብርሃነ፤ የማህበሩ ሰብሳቢ፡፡
እኔም፤ “ቢፈልጉ ስለራስዎ፣ ቢፈልጉ ስለ ድሬዳዋ፣ ቢፈልጉ ስለ ጄክዶ፣ ቢፈልጉ ስለማህበርዎ… የፈለገዎትን ይንገሩኝ!

ለጽሑፍ እሚመቸኝ እንደሰው ካወራን ነው” አልኩዋቸው፤ በአክብሮትም፣ በፍቅርም፡፡
“ከእኔ ልጀምር …እኔ ብርሃነ ጐበና እባላለሁ፡፡ ኢትዮጵያዊ ነኝ!... ያለሁት ድሬዳዋ ነው፡፡ (ድሬደዌ ነዎታ! አልኩ በሆዴ)

የሙያ መሠረተ - ጥናቴ የማህበረሰብ ልማት ነው፡፡ በኃ/ሥላሴ ጊዜ የመጀመሪያ ኮሙኒቲ ዴቬሎፕመንት ኢንስቲቲዩት

ተቋቁሟል፡፡ አዋሳ የህዝብ ዕድገት ተቋም፡፡ ብዙ ፕሮፌሰሮች… እነ ፕሮፌሰር ሥዩም፤ እነ ፕሮፌሰር እንዳልካቸው ወዘተ.

ነበሩ ያኔ፡፡ እኔም አንዱ ባልደረባ ነበርኩ፡፡
“የዱሮው ትውልድ ነዎታ! እኛ የድንጋይ ብርጭቆ ትውልድ የምንለው ነው” አልኳቸው፡፡
“መጀመሪያ፤ የሠራሁት ደግሞ ጋሽና ሰቲት ሰሜን ኤርትራ። ያኔም ኢትዮጵያዊ ነኝ” አሉ - የህዝብ ዕድገት ሹም”፡፡
እኔ ሳቅኩኝና፤ “Great!” አልኩ፡፡
“ከዚያ የተለያየ ቦታ ሠርቼ፣ በመጨረሻ ጡረታ ወጥቼ ወደ ድሬዳዋ ስመጣ፤ ሲ.አር.ዲ.ኤ ነበር እዚህ - NGOዎችን

የማስተባበር ሥራ ይሠራ ነበር፡፡ እስከ አፋር ድረስ ይንቀሳቀሳል፡፡ የCRDA አባላት የነበሩም ያልነበሩም ድርጅቶች

መረብ እየተዘረጋ ነበር፡፡ አቅም እየገነቡ፣ ከመንግሥት ጋር ከኮሙኒቲም ጋር ይሠራሉ፡፡ ሥልጠናም ነበር፡፡ እዚያ ገባሁ።

ሠፊ መረብ ተዘረጋ፡፡
ከእየሩሳሌም የህፃናትና ማህበረሰብ ልማት ድርጅት ጋር የተዋወቅነው ይሄኔ ነው! እዚህ ድሬዳዋ ላይ በተቋቋመው ፎረም

ውስጥ ካሉት ድርጅቶች አንዱ ጄክዶ ነው - እህማልድ። እኔ ፀሐፊ ነኝ የፎረሙ፡፡ (አፋር፣ ድሬዳዋ፣ ሐረሬ ነው) ጄክዶ

እዚህ አካባቢ በጣም ጥሩ ሥራዎች ነበር የሚሠራው! የአቅም ግንባታ ሥራ ይሠራል፡፡ አሳዳጊ የሌላቸው ህፃናት ላይ

ይሠራል። አረጋውያን ላይ ይሠራል - በድሬዳዋ፡፡ ድሬዳዋ  Drought – Prone (ለድርቅ ተጋላጭ)  ከሚባሉት

አካባቢዎች አንዷ ናት። ጐርፍ የሚያጠቃት አካባቢ መሆኗ በጣም የተረጋገጠ ነው፡፡ ይህንን ለመመከት ጄክዶ እጅግ

በጣም ሰፊ ሥራዎች ይሠራል፡፡
የአውሮፓ ህብረት/ የአውሮፓ ኮሚሽን  (EU/EC) ጥያቄ ያቀርባል ስለ Community Based Organizations at a

grass root level ማህበረሰብ -አቀፍ ድርጅቶችን በመሠረታዊ ወለል ደረጃ ማቋቋም፡፡ ማህበረሰብ አቀፍ ድርጅቶች

በጋራ ሆነው ችግራቸውን የሚፈቱበት መንገድ እንዲፈጠር ሃሳብ ይቀርባል ይረቀቃል፡፡ ቀጥታ ተጠቃሚ ራሱ ማህበረሰቡ

እንዲሆን ነው፡፡ ፈንዱ እዛ ላይ ይውላል፡፡ እንደምታውቀው የድሬዳዋ ህዝብ ተግባቢ ነው፣ አዲስ ነገር በቀላሉ

ይገባዋል፤ ምንም ዓይነት ሥራ ተባበር ሲባል ፈጣን ምላሽ ይሰጣል (Socializes, Understands, Cooperates)

በቀላሉ ማህበራዊ ትሥሥር ይፈጥራል፡፡ ይገባባል፡፡ ይተባበራል፡፡ ፓይለት pilot እናርግ የሚል ሃሳብ ተያዘ፡፡

ፕሮጀክቱን ቀርፆ እዚህ መጣና ተወዳድሮ ጄክዶ አሸነፈ፡፡ ይሄኔ እኔ ብቅ አልኩ!
መሠረቱ ራሱ ማህበረሰቡ ሲሆን ልባዊ ልማት ላይ ያተኮረ ይሆናል! አባት እናት አጥተው የተቀመጡ ህፃናትን የእገሌ

ልጅ ከእገሌ ልጅ ብሎ የባሰበትን ተቸጋሪ መርጦ ይረዳል፡፡ አቅፎ እንደእናት እንደአባት እያየ ያሳድጋል፡፡ እኛ አለን

ይላል፡፡
በህይወት ያለውን ማገዝ፣ ሽማግሌውን መጦር፣ ማሳከም፣ ማህበረሰብ - አቀፍ ድርጅት (CBO) እንግዲህ አስፈላጊ

የሆነው ይህንን ለመሥራት ነው፡፡ ይህንን ለማቋቋም ጄክዶ ያገር ሽማግሌዎችን ጥሪ አድርጐ ድሬዳዋ ላይ በዚህ

መጥቻለሁ፤ አለ፡፡ እንዳልኩህ የድሬዳዋ ህዝብ፤ ለውጥ ተቀባይ፣ የሚገባው፣ መደራጀት የሚችል ህዝብ ነው፤ ብለን

መጥተናልና ምን ትላላችሁ?” አለ፡፡ ጥሪ አደረገ፡፡
“እኛኮ የሚያስተባብረን አጥተን ነው!” ሲል ምላሽ ህዝቡ ሰጠ፡፡  አያያዝ ሳይችል ቀርቶ ልጆች አላሳደጊ፣ ሥራ ፈት

ወጣት፣ ወደአልባሌ ቦታና ማጅራት መቺነት እያመራ አደለም እንዴ? አንድ አርጐ እሚያሠራን፣ እሚያደራጀንና መንገድ

እሚያሳየንማ ካገኘን ምን ገዶን?” የሚል መነሳሳት ተገኘ! “እስቲ እናዋጣ፤ አንድ ሁለት ልጅ አሠልጥነን ሥራ

ብናስይዝ…አንዱ አሳዳጊ ጥሩ ሲሆን፣ ሌላው ደህና አሳዳጊ ስላላጋጠመው ከሚጐዳ፤ በጋራ ብናደርገውስ የሚል ነው

መሠረቱ አድልዎ - አልባ fair የሆነ distribution የሀብት - ክፍፍል፡፡ ሰው ተደሰተ፡፡ አመራሩን ተቀበለ፡፡ ጄክዶ

እዚህ ቢሮ ሰጠን እንድናደራጅ፡፡ ዕድሮች፣ ኮኦፕሬቲቭ፣ ቻሪቲም አሉ፡፡ 70፣ 80፣ የሚሆኑ አደራጅ ኮሚቴ መረጡ፡፡

በከተማው ዘጠኝ ቀበሌ ነው ያለው፡፡ ከዛ የተውጣጡ ናቸው፡፡ ቢያንስ በየቀበሌው ሁለት ሁለት ተወካይ 20 ሰዎች።

ህጋዊ የሆነ ያልሆነ፣ የተመዘገበ ያልተመዘገበ፣ አቅም ያለው የሌለው፡፡ በባህላዊ አሠራሩ ውስጥ ያለ ያመራር ችግር ነበር፡፡

መዝገብ የለም፣ ሂሳብ የሚሠራ ሰው የለም ወዘተ…ከዛ ሥልጠና ሰጠን፡፡ በመንግሥት ታወቁ፡፡ ታማኝነት ተፈጠረ፡፡

መዋቅር ተዋቀረ፡፡ ትልቅና ጠንካራ ሆኑ፡፡ ገና በሥልጠናው ሲታይ የልምድ ልውውጥ ከናዝሬት፣ ከደብረዘይት፣ ከአዲሳባ

ተደረገ፡፡
በነዛ ዓይነት ህብረት መፍጠር ተቻለ፡፡ 47 ዕድሮች አሁን 54 ደርሷል ተደራጁ፡፡ በዩኒቨርሲቲ በተጠኑ ጥናቶች

ከመንግሥት ጋርና በራሳቸው ውስጥ ምን ዓይነት መልክ ይኑራቸው? በሚል ተጠና፡፡ System Develop ማኑዋሎች

ተዘጋጁ፡፡ ሥርዓት ያለው መዋቅር ኖረ፡፡ ተመሳሳይ ሥራዎች ይሠራሉ፡፡
ዕድሮች ህፃናትን ያሳድጋሉ፡፡ በጤና ላይ ይሠራሉ፡፡ ጐርፍ ይከላከላሉ፡፡ ኮኦፕሬቲቭስ አሉ፡፡ በትምህርት ላይ ይሠራል።

በምን ደረጃ ላይ ናቸው? ሲባል፤ ይለያያሉ፡፡ Diversified ናቸው፡፡ ሲቪል ሶሳይቲ ናቸው Communication

Network ያስፈልጋል፡፡ በልዩ ልዩ ተግባራት ዙሪያ የተሰባሰቡ ቡድኖችን (Cluster of activities) ማቋቋም አስፈላጊ

መሆኑን አመን፡፡
ሲቪል ሶሳይቲ ናቸው ሁሉም የትምህርት፣ የጤና፣ አካባቢ ጥበቃ ወዘተ፡፡ Network ግን የለንም፡፡ ስለዚህ በይዘት ላይ

የተመሠረቱ ስብስቦች (thematic clusters) ደረጃ፣ partners (አጋር) እንዲሆኑ ማድረግ ዓይነተኛ መንገድ ሆነ፡፡

በመጀመሪያ እንግዲህ ጄክዶ ለዚህ ገንዘብ ሰጠን - ማስጀመሪያ ነው!
የሚያስፈልጋቸውን ነገር፣ ዐይነትና መጠን ዴንማርክ፣ አየርላንድ፣ እንግሊዝ፣ ሆላንድና ኖርዌይ ያሉበት የሲቪል

ማህበረሰብ ፕሮግራም አቋቋምን፡፡ አዲስ ተግባር አመንጪ  (Innovation Action) ተብሎ የተወሰደ ነው፡፡ ወደ

ህብረተሰቡ የሚወርድ ሆኖ፣ በስብስቦቹ መዋቅር የሚመራ ነው፡፡ ተጠንቶ ነው፡፡ 9 ቀበሌዎች ናቸው፡፡ በተግባር ሲታይ

ገጠር ለመሄድ አቅም የለም፡፡ ባጃጅ አለችን፡፡
ዘለቄታው አላቂ ማቴሪያሎች ላይ ነው ጉዳዩና ራሱን በራሱ እሚችልበትን መንገድ ሽተናል፡፡ ለዚች ፕሮግራም

የሚያስፈልገው ዳቦ ቤት ነው? ሽመና ነው? መክፈት ያለበት ወዘተ እያልን ቋሚ ነገር እያሰብን ነው፡፡ እንዳልኩህ ነው።

በልመና ከሆነ፣ ልብሷ ታልቃለች፣ ደብተሯም ታልቃለች፣ ስለዚህ እየለመንክ ዘላቂነት የለም፡፡ 2011 መጨረሻ ላይ

ጀምረን ነው የቀረጽነው፡፡ ስኬታማ ሆነናል በ2013!”
“ዕድሮችን ማግኛ መንገዳችሁ ምንድን ነው?”
“ቦርድ አባላት አሉ፡፡ በየ2 ዓመቱ የሚቀየሩ፡፡ በየቀበሌው ያሉ የኛ አባላት የራሳቸው ፕላት ፎርም አላቸው፡፡ ያላቸው

ችግር ካለ፣ ከመንግሥት ጋራም መወያያ፤ የራሳቸው መድረክ አላቸው። እዛ ሲሰሩ ከመንግሥት ጋር ነው፡፡ ማነው

መንግሥት? ቀበሌ ነው፡፡ ከመንግሥት ጋር በጋራ እንሠራለን፡፡ ስለዚህ በስብስብ  ኮሚቴዎች እንገናኛለን፡፡ ዕድር፣

ቀበሌ፣ cluster ኮሚቴ ያረጋግጡልናል፡፡ አሁን ባጃጅ የሚነዱ ስልጠና ላይ ነን
ምንም ሳይኖረን ሠርተናል! አሁን የተሻለ መሥራት እንችላለን፡፡ ቀስ በቀስ ነው እዚህ የደረስነው፡፡
“ስንት ዓመትዎ ነው” አልኳቸው ስለማንነታቸው ላውቅ፡፡
“68”
“በጣም ጠንካራ ነዎት ማለት ነው!”  
“የተፈጥሮ ችግር አያስቀምጥህም፡፡ ጋቢና ጭራ ይዘህ ቤትህ ከመቀመጥ ይልቅ፤ እዚህ መሥራት፤ ህይወትህን

ያድስልሃል፡፡ አንዳንድ ሰው ጡረታ ትወጣለህ ሲባል መንፈሱ ይወድቃል! እኔ አመመኝ ማለት አልወድም! ተጓዳኝ

ሥራዎች አሉን፡፡”
“ጄክዶ ያግዛችኋል አሁንም?”
“Phase – out አርጓል ግን አሁንም ኮንታክት አለን፣ አሁን የህብረተሰብ እግር ኳስ አለ፡፡ አለንበት፡፡ ፈንድ ተገኝቷል

ወጣቶችን ያገናኛል፡፡ የሶስት ሪጂኖች ነው - ሐራሪ፣ ሱማሌና አፋር፡፡ የሰላምና የአንድነት ፕሮጀክት ነው፡፡ ጄክዶ

ወሰደው። ለእኔ ሰጠኝ፡፡ ባገር ሽማግሌዎች ለነዚህ ወጣቶች ትምህርት ይሰጣል፡፡ ፓንፍሌት ይበተናል፡፡
ትምህርት  በእግር ኳሱ በእረፍት ጊዜ ይሰጣቸዋል ወዘተ የኦሮሞ፣ የአማራ፣ የደቡብ፣ የሱማሌ፣ የአፋር ከተለያዩ የብሔር

ብሔረሰቦች የተውጣጡ ናቸው፡፡ በየቋንቋው ነው የሚቀርብላቸው፡፡ ገና 3ኛና 4ኛ ዙር ይቀራል፡፡ ወንድማማቾች

መሆናቸውን ይማማሩበታል፡፡ ሌላ ደግሞ፤
Ethiopian. social accountability የሚባል ፕሮግራም አሁንም ከጄክዶ ጋር አለ፡፡ ለገጠር ፤ ውኃ፣ ፅዳት፣ ጤና፣

ትምህርት… የኢትዮጵያ መንግሥት ከዓለም ባንክ የሚያገኘው ፈንድ ነው ህዝቡ የራሱ ማድረጉን እናያለን፡፡ መንግሥት

እና ኮሙኒቲ መመዘን አለበት! ሸንጐl አቋቁመናል፡፡ ተጓዳኝ ሥራዎች ተቋቁመዋል፡፡ የአረጋውያንና የደካማ ሰዎች

ፌዴሬሽን በኢትዮጵያ ደረጃ ይቋቋማል! ወደፊት ወደ አገር አቀፍ ደረጃ እናሳድጋቸዋለን፡፡
“EDDC የብርሃነ ጐበና ታላቅ ፍሬ ነው፡፡ በ68 ዓመት እንዲህ ያለ ሥራ ከባድ ነው፡፡ ለመሆኑ እነዚህን ሁሉ ኮሚቴዎች

ለመምራት ጊዜ ይበቃዎታል?”
“አይ የፕላኒንግ ጉዳይ ነው እንደዚህ እንዳሁኔ ድንገተኛ ነገር ሲያጋጥም ነው እንጂ እስካሁን በእቅዴ ሐዲድ ላይ ነው

እየሄድኩ ያለሁት፡፡ በጥንቃቄ ነው የምይዘው፡፡ በሁለት ሣምንት ወይም በወር አረጋግተህ ትይዘዋለህ፡፡ የምክር ቤት

አባል ነኝ… የሰፈሬ ዕድር አባል ነኝ… አቀናጃቸዋለሁ… የራሳችን ከሆነ በአጀንዳችን ይሠራል!...”
“ስንት ልጆች አሉዎ?”
“አምስት አሉኝ ሁሉም ደህና ናቸው፡፡ ራሳቸውን ችለዋል፡፡ ሥራ ላይ ናቸው፡፡ አንዱ ጐረምሳ አለ… አሁን ነው

እሚጨርሰው፡፡ ባለቤቴም ሠራተኛ ነች፡፡ በሥራ ጉዳይ አዲሳባ ነች፡፡ እኔ እዚህ ነኝ፡፡ በፕሮሞሽን ነው የሄደችው፡፡ ያ

ደግሞ አይጠላም - የማኔጅመንት ሰው ነች እዛ”
“ማህበራዊ መስተጋብሩዋ  እንዴት ነው?”
“የሚገርም ነገር ነው፡፡ ባልና ሚስት ካንድ ውሃ ይቀዳል ነው…ፖስታ ቤት ስሄድ እትዬ ደህና ናት እያሉ ተጠምጥመው

ይስሙኛል”
“ኢትዮ - ውስጥ ያላዩት ቦታ አለ?”
“ባሌና ኤሊባቦር”
ሥራ አስኪያጁ  ይሄኔ መጣ፡፡
“ባሌን ኮፈሌን አላውቃትም አሉኝኮ አቶ ብርሃነ?” ስለው፤
“ኮሙኒቲ ዴቬሎፕመንት ምንጩ እዛ ነው፡፡ ሐረርጌ The moving Atlas ይባላል፡፡ ዋናው ነገር ሐረርጌ ነው፡፡”
“ጐሙጐፋን በብዙ ሠርቼበታለሁ” አሉ አቶ ብርሃነ፡፡
ደራሲው ፀጋዬ ገ/መድህን፤  “በከርሞ ሰው” ላይ፤ አብዬ ዘርፉ “እቺን ሠርቼባታለሁ” ይላሉ፤ ግድግዳ ላይ

ወደተሠቀለችው ጠመንጃ እያሳዩ፡፡ አቶ ብርሃነ “ሠርቼበታለሁ” ሲሉ የመጣብኝ ስሜት የዚህ አይነት ነው፡፡
“እዚህ አገር እርግጠኛ የማትሆንበት ነገር (Uncertainty ው) ብዙ ነው፡፡ ወዳጄ ለትራንስፖርት መኪና ላይኖር

ይችላል። መኪናው ሲገኝ ጐማው ተበላሽቷል - መቀየር አለበት፡፡ ጐርፉ ራሱ አንድ Uncertainty ነው” አለ፡፡
ፀጋዬ ገብረመድህን “እንኳን ለዓመት ጉድ አበቃን” የሚል ግጥም አለው፡፡ የፍልውሃን ዓመታዊ ጐርፍ መጥለቅለቅ

አስመልክቶ የፃፈው ነው፡፡ ምነው የድሬዳዋን ጐርፍ ባየና በፃፈ” አልኩ፡፡
እኔም የድሬዳዋውን አስመልክቼ አንድ ግጥም ጽፌአለሁ። ቆይ ሁለቱንም ግጥሞች ለአንባቢ አቀርባቸዋለሁ  አልኩኝ

በሆዴ!
(የድሬዳዋ  ጉዞዬ የመጨረሻው ክፍል ይቀጥላል)

Read 3565 times