Print this page
Saturday, 09 November 2013 10:02

አየር መንገድ 400 ሰዎች የሚጭን አውሮፕላን ተረከበ

Written by 
Rate this item
(3 votes)

               የኢትዮጵያ አየር መንገድ ካዘዛቸው አራት ግዙፍ ቦይንግ 777300ER አውሮፕላኖች የመጀመሪያውን ትናንት የተረከበ ሲሆን፤ ለቦይንግ አውሮፕላኖች የሚያገለግሉ የኤሌክትሪክ መስመሮችን መፈብረክ ይጀምራል ተባለ፡፡ አየር መንገዱ በበረራ ታሪኩ 400 ሰዎች የመያዝ አቅም ያለው አውሮፕላን ሲረከብ የመጀመሪያው ሲሆን፣ አውሮፕላኑ ብዙ መንገደኞችን ለማስተናገድ እንደዋሽንግተን ዲሲ፣ ዱባይና ጉዋንዙ (ቻይና) የመሳሰሉ በተጨማሪ ረዥም ርቀት ያለማቋረጥ መጓዝ እንደሚችል ታውቋል፡፡

በአለም በግዝፈታቸው በሚታወቁና በጄኔራል ኤሌክትሪክ ኩባንያ የተሰሩ ኢንጂነሮች የሚንቀሳቀሰው ይሄው አውሮፕላን፣ በአራት ረዣዥም ክፍሎች በሦስት ረድፍ የተሳፋሪ መቀመጫዎች ሰትሮ የያዘ ነው፡፡ መቀመጫዎቹ ምቹ፣ ቦታው ሰፊና ጣሪያው ከፍ ያለ ነው፡፡ የአውሮፕላኑ አብራሪ ካፒቴን ካሌብ ማሞ፣ ሲያትል ከሚገኘው የቦይንግ ኩባንያ ማዕከል እስከ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ለ15 ሰዓታት በመብረር መድረሳቸውን ገልፀው፤ አውሮፕላኑ ዘመናዊ ከመሆኑም በላይ በዘመኑ የቴክኖሎጂ ውጤቶች የተፈበረከ ስለሆነ ለመንገደኞች ከፍተኛ እንደሚሰጥ ተናግረዋል፡፡ የአሜሪካ አምባሳደር ፓትሪሺያ ሃሳላክ በበኩላቸው የቦይንግ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግንኙነት ጠንካራ መሆኑን በመጥቀስ፣ አየር መንገዱ ለቦይንግ አውሮፕላኖች የሚያገለግሉ የኤሌክትሪክ መስመሮችን መፈብረክ እንደሚጀምር ተናግረዋል፡፡

Read 2912 times
Administrator

Latest from Administrator