Print this page
Saturday, 02 November 2013 11:54

ወፍ እና ማለዳ

Written by 
Rate this item
(7 votes)

እንኳንስ ችግኙ፣ ሰዎች የተከሉት
ሥር ይይዝ ነበረ፣ አዕዋፍ የዘሩት፡፡
ዘንድሮ ግን ወፎች፣ እንኳንስ ሊዘሩ
ናፍቆኛል ማለዳ፣ መስማት ሲዘምሩ፡፡
ወፎች ከማለዳ
በምን ተቃቃሩ?
ፅልመቱ ሲገፈፍ
እንዳላበሠሩ፤
ማዜም ተስኗቸው
ተዘግቶ ጀንበሩ
ወደሚነጋበት
ወዴትስ በረሩ?!

እችልሻለሁ!!
ስለ እውነት እልሻለሁ፣
ስለወደድኩሽ እችልሻለሁ!
የአያሌ ሞገደኞች ድምር፣ በአንድነት ተጨፍልቆ
ከሰብእናሽ ተላቁጧል፤ አድርጎሻል የሴት ኅልቆ፡፡
ካልተገሩ ባህርያት፣ እስከጠፋ ያለም ፍጥረታት
ነፍስያና አመላቶች ተጎንጉነው ያየሁባት
ብትሆኚም ብቸኛዋ፣ እስከዛሬ ያፈቀርኳት
እልሻለሁ “አያሌዎች”፣ ምስክር ነኝ ስለ እውነት!
ይህም ቢሆን … “እችልሻለሁ!”
ባንዲት ነፍሴ እምላለሁ!
ፍቅር ቀድሞ ገሎኛል፣ ስለምንስ እፈራለሁ?
የምታደርጊውን አድርጊኝ፣ ይኸው ፊትሽ ቆሜያለሁ
(“ሀ-ሞት” ከተሰኘው
የሄኖክ ስጦታው የግጥም መድበል
የተወሰደ - 2005)

Read 5143 times
Administrator

Latest from Administrator