Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 26 November 2011 09:02

የሙዚቃ ባለሙያ ደረጄ መኮንን ቀብር ሐሙስ ተፈፀመ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ባለፈው ሰኞ በድንገተኛ ሕመም ሕይወቱ ያለፈው ታዋቂው የሙዚቃ ባለሙያ ደረጄ መኮንን በሥራዎቹ እንደሚዘከር ወዳጆቹ ገለፁ፡፡ የአርቲስቱ የቀብር ሥነስርዓት ከትላንት በስቲያ ደረጄን ለመዘከር በተዘጋጀ የሕይወት ታሪኩ በኢትዮጵያ ዘመናዊ የሙዚቃ ታሪክ ውስጥ የራሱን አሻራ ማተም የቻለ የኪነጥበብ ሰው ነው ሲሉ የዘከሩት የሕይወት ታሪክ አዘጋጆች በ14 ዓመቱ ከ”አይቤክስ” ሙዚቃ ቡድን ጋር መስራት መጀመሩን እና ለዚህም ታላቅ ወንድሙ ቴዎድሮስ መኮንን (ቴዲማክ) ቤት ውስጥ ፒያኖ ሲጫወት ማየቱ ራሱን እንዳስተማረ አውስተዋል፡፡

ደረጄ መኮንን ከ”አይቤክስ” የሙዚቃ ቡድን ሌላ ከ”ሸበሌ”፣ ከ”ዘመኮንንንስ”፣ “ጊዜ”፣ እና ሌሎች ቡድኖች ጋር አብሮ የሰራ ሲሆን በ1977 ዓ.ም ሺካጎ ላይ የተመሠረተው የ”ዳሎል” የሙዚቃ ቡድን መስራች አባል ነው፡፡ ደረጄ ካቀናበራቸውና የሙዚቃ መሳርያ ከተጫወተባቸው ታዋቂ ዘፈኖች መካከል የኤፍሬም ታምሩ የመጀመርያ አልበም “ጀማዬ”፣ የአስቴር አወቀ “ሰኞ እለት”፣ የእጅጋየሁ ሽባባው “አቦ ሸማኔ” እንዲሁም ከጥላሁን ገሠሠ፣ ማህሙድ አህመድና ከቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ጋ “መሀረቤ” የተሰኘ አዲስ ሥራ ሰርቶ ማጠናቀቁም ተገልጿል፡፡

 

Read 2804 times Last modified on Saturday, 26 November 2011 09:04