Saturday, 26 October 2013 13:23

በመኪና አደጋ የ7 ሰዎች ህይወት አለፈ

Written by  መልካሙ ተክሌ
Rate this item
(2 votes)

ሃያ ስምንት ሰዎችን አሳፍሮ ከጅጅጋ ወደ ድሬዳዋ ሲጓዝ የነበረ ካቻማሊ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቢስ ተገልብጦ አምስት ሰዎች ወዲያውኑ ሲሞቱ፣ ሁለቱ በህክምና ላይ እያሉ ሕይወታቸው አለፈ።
የድሬዳዋ ፖሊስ ህዝብ ግንኙነት ዲቪዥን ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ገመቹ ካቻ ለአዲስ አድማስ እንደገለፁት፣ አደጋው ሐሙስ ከሰዓት በኋላ ስምንት ሰዓት አካባቢ የደረሰ ሲሆን ከሞቱት ሰዎች ሌላ አስራ አራት ሰው በፅኑ፣ ስድስት ሰዎች በቀላል መቁሰላቸውን አስረድተዋል፡፡
ፖሊስ የአደጋውን መንስኤ በማጣራት ላይ ሲሆን፣ መኪናው አለአግባብ ወደቀኝ ሲታጠፍ አደጋው መድረሱንና የመኪናው ሹፌር በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራው መቀጠሉን ገልጿል፡፡ በዚሁ ሳምንት በመቀሌ መስመር የሕዝብ ማመላለሻ መኪና ገደል ገብቶ 26 ሰዎች መሞታቸው ይታወሳል፡፡

Read 1987 times