Print this page
Saturday, 26 October 2013 13:14

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሬዲዮ ጣቢያ ከፈተ

Written by  ማህሌት ፋሲል
Rate this item
(0 votes)

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በጋዜጠኝነትና ኮሙኒኬሽን ት/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ የሬድዮ ጣቢያ ከፍቶ ስርጭት ጀመረ፡፡ የጣቢያው ስራ አስኪያጅ አቶ አቤል አዳሙ ለአዲስ አድማስ እንደገለፁት፤የዩኒቨርስቲው የሬዲዮ ስርጭት ከጀመረ 10 ቀኑ ሲሆን በጋዜጠኝነት የተመረቁ አምስት የቀድሞ ተማሪዎቻቸውን በጊዜያዊነት ቀጥረው እያሰሩ ይገኛሉ፡፡ ሬዲዮ ጣቢያው በአሁኑ ሰአት ሙዚቃዎችን ብቻ እያስተላለፈ ቢሆንም በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ዜናዎችንና ማህበራዊ ጉዳዮችን የሚዳስስ ፕሮግራም ማስተላለፍ እንደሚጀምር አቶ አቤል ገልፀዋል፡፡ የሬዲዮ ጣቢያው አላማ ምን እንደሆነ የተጠየቁት ሥራ አስኪያጁ፤ “ዩኒቨርስቲዎች ለአገር የሚያደርጉትን አስተዋፅኦ ለማዳበር ነው” ብለዋል፡፡ ከጠዋቱ አንድ ሰዓት እስከ ቀኑ ስምንት ሰዓት በአየር ላይ የሚቆየው የሬዲዮ ስርጭት፤ሁኔታዎች ሲስተካከሉ የሙሉ ቀን ስርጭት እንደሚሆን የተናገሩት አቶ አቤል፤ያኔ ለሌሎች ጋዜጠኞችም የስራ እድል እንደሚፈጥር ገልፀዋል፡፡
ዩኒቨርስቲው የሬዲዮ ጣቢያውን የከፈተው በቀድሞው የማስታወቂያ ሚኒስቴር ውስጥ ሲሆን መስሪያቤቱ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጋዜጠኝነትና ኮሙኒኬሽን ት/ቤት ከሆነ ወዲህ፤ ጣቢያውን ለተማሪዎች ተግባራዊ ልምምድ ሲጠቀምበት ቆይቷል፡፡ ሬዲዮ ጣቢያው ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያው ሲሆን የአዋሳ፣ አለማያ፣ ለቀምት፣ ጅማና ደብረታቦር ዩኒቨርሲቲዎች የሬዲዮ ጣቢያ እንዳላቸው ይታወቃል፡፡

Read 1769 times