Saturday, 26 October 2013 13:12

11ኛው ብሄራዊ “የሳቅ ቀን” ሀሙስ ይከበራል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

ለሁለት ደቂቃ ሁሉም እንዲስቅ ተጋብዟል
“ሳቅ ለሁሉም ማህበር ኢትዮጵያ” የፊታችን ሀሙስ ረፋድ ላይ 11ኛውን ብሔራዊ “የሳቅ ቀን” ያከብራል፡፡ ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ጀምሮ በማህፀን ውስጥ እስካለ ህፃን ድረስ በዕለቱ ጠዋት ከአራት ሰአት ከሰላሳ እስከ አራት ሰዓት ከሰላሳ ሁለት ድረስ ለሁለት ደቂቃ ሁሉም እንዲስቅ ማህበሩ ጥሪ አቅርቧል፡፡
ላለፉት አስር አመታት “የሳቅ ቀን”ን በተለያዩ የክልል ከተሞች ያከበረው ማህበሩ፤ ዘንድሮም 11ኛውን የሳቅ ቀን በአዲስ አበባ ከተማ ባህል ማዕከል “የደስታ፣ የጤና እና የለውጥ ማሳ የሆነውን ልባችንን በሳቅ እንኮትኩት” በሚል መሪ ቃል ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 6፡30 ሰዓት ድረስ ለማክበር ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ማህበሩ አስታውቋል፡፡
ሳቅ በአለማችን ቁጥር አንድ የሆነውን ጭንቀትን ለመቀነስ ዋነኛ መፍትሔ እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን፤ ህዝቡም ከጓደኛው፣ ከቤተሰቡ እና ከጐረቤቱ ጋር ጤናማ ሳቅን መሳቅ ቢያዳብር በህይወቱ፣ በስነ - ልቦናው እና በስራው አካባቢ ጤናማ እና ውጤታማ ይሆናል ተብሏል፡፡

Read 1099 times