Saturday, 07 September 2013 09:53

ኮካ ኮላ በፕላስቲክ መያዣ ለገበያ ቀረበ

Written by  መልካሙ ተክሌ
Rate this item
(0 votes)

የኢስት አፍሪካን ቦትሊንግ ኩባንያ በ800 ሚ.ብር ተጨማሪ ግንባታ የኮካ ኮላ ምርቶቹን በፕላስቲክ መያዣ ማቅረብ ጀመረ፡፡ ምርቶቹ የሚቀርቡት በግማሽ ሊትር እና በአንድ ሊትር ተኩል የፕላስቲክ መያዣ ሲሆን፣ በቀን 750ሺህ ያህል የማምረት አቅም አለው፡፡
ለአዲስ ግንባታ የዋለው ገንዘብ የረዥም ጊዜ የማስፋፊያ ኢንቨስትመንት አንድ አካል እንደሆነ የጠቀሱት የኮካ ኮላ የኢትዮጵያ ተወካይ ዳሬክተር ግሬግ ጆንሰን፤ ኢንቨስትመንቱ እንደሚቀጥል ማክሰኞ በአፍሪካ ህብረት በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል፡፡
በአዲስ አበባና በድሬዳዋ ካሉት የኮካ ኮላ ምርት ፋብሪካዎች በተጨማሪ፣ በባህርዳር ሦስተኛ ፋብሪካ ለማቋቋም መሬት መረከቡንም ገልፀዋል፡፡

Read 12177 times