Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 19 November 2011 14:44

“ድንበር” እና “ቴክ ኢት ኢዚ” ፊልሞች ይመረቃሉ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

አንኮበር ፊልም ፕሮዳክሽን የግርማ አለማየሁን ድርሰት በፋሲል ግርማ አዘጋጅነት ወደ ፊልም የቀየረ ሲሆን ይኸው ፊልም ነገ በአዲስ አበባና ለምርቃቱ በተመረጡ የክልል ከተሞች ይመረቃል፡፡ በኢትዮጵያና ኤርትራ ግጭት ዙርያ በሚያጠነጥነው ልብ አንጠልጣይ አክሽን አሳዛኝ የጦርነት ፊልም ላይ አርቲስት ፋንቱ ማንዶዬ፣ አልማዝ ኃይሌ፣ ኤልያስ ሻፊ፣ እንግዳሰው ሃብል፣ ራሄል ከበደ፣ መስፍን አድማሱ እና ሌሎችም የተሳተፉ ሲሆን የ90 ደቂቃ ፊልሙን ሰርቶ ለማጠናቀቅ ስድስት ዓመታት እንደፈጀ ማወቅ ተችሏል፡፡ በሌላም በኩል፤ ታሪኩ መኮንን የፃፈውና አንድነት ዳኘው ያዘጋጀውን “ቴክ ኢት ኢዚ” ሥነ ልቦናዊ ፊልም ዘታርያን መልቲ ሚዲያ ፊልም ፕሮዳክሽን ዛሬ በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች ያስመርቃል፡፡ የ100 ደቂቃ ፊልሙን ለመስራት ስድስት ወራት የፈጀ ሲሆን፤ እመቤት ወልደገብርኤል፣ ሰላምሁን አስራት፣ ሃና ዶዳ፣ እመቤት ካሳ፣ አስቻለው ዘለቀ፣ ኦርዮ አስፋው ይተውኑበታል፡፡

Read 4094 times