Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 19 November 2011 14:39

ጄሎ 4ኛ ባሏን አጨች

Written by 
Rate this item
(0 votes)

የ42 ዓመቷ ጄኒፈር ሎፔዝ ከ19 ዓመት ታናሿ ስማርት ካስፐር ጋር መተጫጨቷ ተገለፀ፡፡ ዳንሰኛዋ ከሆነው ከዚህ የ22 ዓመት ወጣት ጋር 4ኛ ትዳሯን ልትመሰርት እንደምትችል ቲኤምዜድ የተባለ ጉድጎልጋይ ድረገፅ አጋልጧል፡፡ ጄሎ ከላቲኑ ድምፃዊ ማርክ አንቶኒ ጋር ለዓመታት የቆየችበትን ትዳር ፍቺ ከፈፀመች 3 ወር ቢሆናት ነው፡፡ ጄሎ አራተኛ ትዳሯን ከምትመሰርተው ካስፐር ጋር በቬንስ ጣሊያን ባለፈው ሳምንት ቀለበት በማሰር ተጫጭተዋል፡፡
የራሷን የሪያሊቲ ሾው ለማዘጋጀት እየተሯሯጠች ያለችው ጄኒፈር ሎፔዝ በፖፕ ሙዚቃ ላይ ያላት የበላይነት ከግዜ ወደ ግዜ እየወረደ መጥቷል ያለው ዘፒፕል ማጋዚን በበኩሉ በ42 ዓመቷ በፋሽኗና በተስተካከለ ሰውነቷ እንደ 20 ዓመት ኮረዳ የምታማልል ናት ብሏል፡፡

Read 3895 times