Saturday, 27 July 2013 13:30

በአይሲቲ እና በባንክ ዙሪያ ዓለምአቀፍ ጉባኤ ይካሄዳል

Written by  መልካሙ ተክሌ
Rate this item
(0 votes)

ኢትዮጵያ፣ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ (አይሲቲ) የባንክ አገልግሎት ለማቀላጠፍ በሚያመበረክተው አስተዋጽኦ ላይ የሚመክር ዓለምአቀፍ ስብሰባ በመጪው አርብ ታስተናግዳለች፡ “Harnessing Africa’s Digital Future” በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው ጉባኤ በኢትዮጵያና በሌሎች የምስራቅ አፍሪካ አገራት ውስጥ የባንክ አገልግሎትን በሚመለከት የአይሲቲ አማራጮችንና የቢዝነስ እድሎችን ይፈትሻል ተብሏል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ፣ በአዲስ አበባ ሸራተን ሆቴል በሚካሄደው በዚሁ ጉባኤ ላይ፣ በኤሌክትሮኒክስ ቴክኖሎጂ ቀልጣፋ የባንክ አገልግሎት ከማቅረብ ጐን ለጐን፣ ባንኮች የደንበኞቻቸውን እምነት ጠብቀው እንዴት መጓዝ እንደሚችሉ ይመከርበታል፡፡ የገንዘብ ማጭበርበር ስጋቶችን ለመቀነስ በሚያስችሉ መንገዶች ላይም ውይይት ይካሄዳል፡፡

Read 16300 times