Monday, 27 May 2013 15:09

“ድርሳነ ደም” ለኤርትራ ስደተኞች በነፃ ይታደላል

Written by  መልካሙ ተክሌ
Rate this item
(1 Vote)

በኤርትራዊው ፀሐፊ ሚካኤል እምባዬ የተዘጋጀው “ድርሳነ ደም” የፖለቲካዊ ታሪክ መጽሐፍ ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ ተመረቀ፡፡ አዲስ አበባ በሚገኘው አክሱም ሆቴል የተመረቀውን መጽሐፍ ለማዘጋጀት ከሁለት ዓመት በላይ እንደፈጀበት ደራሲው ለአዲስ አድማስ ገልፀዋል፡፡ ለደራሲው ሁለተኛ የሆነው ባለ 304 ገጽ መጽሐፍ በምርቃቱ እለት በ100 ብር የተሸጠ ሲሆን በኢትዮጵያ ለሚገኙ የኤርትራ ስደተኞች በነፃ እንደሚታደል ታውቋል፡፡

Read 1748 times