11 ዓመታትን በዘገየው የዶር ድሬ አልበም የዌስት ኮስት በርካታ ራፕሮች የተካፈሉባቸው 4 ዘፈኖች እንደተካተተበት የጠቆመው ኤምቲቪ ኒውስ፤ ስኑፕ ዶግም አብረውት ከሰሩት ራፐሮች መካከል እንደሚገኝበት ዘግቧል፡፡ በአሜሪካ የራፕና ሂፕሆፕ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ በቀዳሚነት ከሚጠቀሱት አንዱ የሆነው ዶር ድሬ፤ እነ ስኑፕ ዶግ፤ ኤሚነምና ፊፍቲ ሴንትን በሙዚቃ አሳታሚ ኩባንያው በማሰራት በራፕና ሂፕሆፕ እያሰለጠነ ለስኬት ያበቃ ነው፡፡ በአዲሱ የፈረንጆች ዓመት 2012 ይወጣል ተብሎ በሚጠበቀው አልበሙ ዶር ድሬ፤ የራፕና ሂፕሆፕ ገበያን የመቆጣጠር ፍላጐትእንዳለው ተጠቁሟል፡፡አፍተርማዝ ኢንተርቴይመንት የተባለ የሙዚቃ አሳታሚ ኩባንያ ባለቤት የሆነው የ46 ዓመቱ ዶር ድሬ፤ በርካታ አዳዲስ ራፐሮችን ወደ ኢንዱስትሪው ለማስገባት ዝግጅት ማድረጉንም ተናግሯል፡፡