ፎርብስ ደረጃውን ለማውጣት ተዋናዮች በሰሩባቸው ፊልሞች ምን ያህል እንደተከፈላቸው፤ ፊልሞቻቸው በምን ያህል ሲኒማዎች እንደታዩ እና ምን ያህል ገቢ እንደተገኘባቸው አስልቷል፡፡ድሪው ባሪሞር በመጨረሻ የሰራቻቸው ሁለት ፊልሞች “ኤቭሪ ባዲ ፋይን› እና ‹ላኪ ዩ› በድምሩ 24 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ቢገኝባቸውም ለእያንዳንዳቸው 15 ሚሊዮን ዶላር ተከፍሏት መተወኗን የፎርብስ መረጃ ጠቁሟል፡፡ድሪው ባሪሞር በመሪ ተዋናይነትና ዲያሬክተርነት የሰራቻቸው ሁለት ፊልሞች ‹ጎይንግ ዘ ዲስታንስ› እና ‹ዊፕ ኢት › የበጀታቸውን ግማሽ እንኳን ገቢ አልተገኘባቸውም፡፡በዚሁ የፎርብስ አክሳሪ ተዋናዮች ደረጃ ሰሞኑን ኦስካር ማስተናገድ አልፈልግም ያለው ኤዲ መርፊ በተከፈለው 1 ዶላር 2.75 ዶላር ገቢ ይገኝበታል ተብሎ ሁለተኛ ደረጃ አግኝቷል፡፡ ባለፉት ሁለት ዓመታት ተመሳሳይ የደረጃ ዝርዝርን ሲመራ የነበረው ኮሜድያኑ ዊል ፋሬል 3.50 ዶላር እንዲሁም ዴንዝል ዋሽንግተን 4.25 ዶላር በተከፈላቸው 1 ዶላር በማስገባት 3ኛና አራተኛ ደረጃን ይዘዋል፡፡