Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 12 November 2011 08:10

ሆሊውድን ለሚያከሥሩ ተዋናዮች ደረጃ ወጣ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ድሪው ባሪሞር የሆሊውድ ፊልም ሰሪዎችን በኪሳራ ጎድተዋል የተባሉ ተዋናዮች ደረጃን በአንደኛነት በመምራት ላይ እንደሆነች ፎርብስ መጽሄት አስታወቀ፡፡የ36 ዓመቷ ድሪው ባሪሞር፤ በተከፈላት 1 ዶላር ከ40 የአሜሪካ ሳንቲም ብቻ እያስገባች መሆኑን የጠቀሰው ፎርብስ መፅሄት ተዋናይቷ ተፈላጊነቷ ባለፉት 2 ዓመታት ቀንሷል ብሏል፡፡

ፎርብስ ደረጃውን ለማውጣት ተዋናዮች በሰሩባቸው ፊልሞች ምን ያህል እንደተከፈላቸው፤ ፊልሞቻቸው በምን ያህል ሲኒማዎች እንደታዩ እና ምን ያህል ገቢ እንደተገኘባቸው አስልቷል፡፡ድሪው ባሪሞር በመጨረሻ የሰራቻቸው ሁለት ፊልሞች “ኤቭሪ ባዲ ፋይን› እና ‹ላኪ ዩ› በድምሩ 24 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ቢገኝባቸውም ለእያንዳንዳቸው 15 ሚሊዮን ዶላር ተከፍሏት መተወኗን የፎርብስ መረጃ ጠቁሟል፡፡ድሪው ባሪሞር በመሪ ተዋናይነትና ዲያሬክተርነት የሰራቻቸው ሁለት ፊልሞች ‹ጎይንግ ዘ ዲስታንስ› እና ‹ዊፕ ኢት › የበጀታቸውን ግማሽ እንኳን ገቢ አልተገኘባቸውም፡፡በዚሁ የፎርብስ አክሳሪ ተዋናዮች ደረጃ ሰሞኑን ኦስካር ማስተናገድ አልፈልግም ያለው ኤዲ መርፊ በተከፈለው 1 ዶላር 2.75 ዶላር ገቢ ይገኝበታል ተብሎ ሁለተኛ ደረጃ አግኝቷል፡፡ ባለፉት ሁለት ዓመታት ተመሳሳይ የደረጃ ዝርዝርን ሲመራ የነበረው ኮሜድያኑ ዊል ፋሬል 3.50 ዶላር እንዲሁም ዴንዝል ዋሽንግተን 4.25 ዶላር በተከፈላቸው 1 ዶላር በማስገባት 3ኛና አራተኛ ደረጃን ይዘዋል፡፡

 

Read 3562 times Last modified on Saturday, 12 November 2011 08:11