Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 12 November 2011 08:05

ዲካርፒዮ ለኦስካር ሽልማት እንዲታጭ ተጠየቀ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ሊዮናርዶ ዲካርፒዮ ሰሞኑን ለእይታ በበቃው አዲስ ፊልሙ ያሳየው የትወና ብቃት ለኦስካር እንዲያሳጨው የሚጠይቁ መብዛታቸውን ዘ ሆሊውድ ሪፖርተር አስታወቀ፡፡ ዲካርፒዮ መሪ ተዋናይና ፕሮዱዩሰር ሆኖ ከዲያሬክተሩ ክሊንት ኢስትውድ ጋር “ጄ ኤድጋር” የተባለውን ፊልም ሰርቷል፡፡ ዲካርፒዮ የአንጋፋ ገፀባህርያትን ሚና መጫወት ማብዛቱን የገለፀው የኤምኤስኤንቢሲ ዘገባ፤ ተዋናዩ ያለው የልጅ ፊት ገፅታ የሆሊውድ አንጡራ ሃብት አድርጐታል ብሏል፡፡

ባለፈው ዓመት ‹ሻተር አይስላንድ› እና ‹ኢንሰፕሽን› በተባሉ ፊልሞች 1.2 ቢሊዮን ዶላር ያስገባው ዲካርፒዮ፤ ዘንድሮ ዓመታዊ ገቢው 77 ሚሊዮን ዶላር የደረሰ ሲሆን ከተዋናዮች ከፍተኛው ባለገቢ አድርጐታል፡፡ ዲካርፒዮ በአንድ ፊልም በአማካይ 80 ሚሊዮን ዶላር ገቢ እንደሚያስገኝ ያመለከተው ናሽ ኢንፎርሜሽን የተባለ ድረገፅ፤ በስራ ዘመኑ በተወነባቸው ከ50 በላይ ፊልሞች ከ4.8 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ማድረጉን ያመለክታል፡፡

 

Read 3630 times Last modified on Saturday, 12 November 2011 08:09