Saturday, 27 April 2013 10:29

ከኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት በ6 ወር ከ97 በላይ ሠራተኞች ለቀቁ

Written by  በጋዜጣው ሪፖርተር
Rate this item
(4 votes)

ከኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ ከ97 በላይ ሠራተኞች የለቀቁ ሲሆን የሰው ሃብት አስተዳደር ክፍል ለሠራተኞች የሥራ ልምድና መልቀቂያ በመስጠት መጠመዱን ምንጮች ጠቆሙ፡፡ ሠራተኞች የሚለቁት በአስተዳደር በደል መሆኑን ሲገልፁ ድርጅቱ በበኩሉ “ሠራተኞች በጡረታና በሞት እንጂ ሌላ ምክንያት የላቸውም” ብሏል፡፡

ድርጅቱ አንዳንድ ጥቅማጥቅምና የማትጊያ አሠራሮችን በመጠቀም ሠራተኞችን ይዞ ሊቆይ ቢሞክርም እንዳልተሳካለት ምንጮች ይናገራሉ፡፡ የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ደመረ አሠፋ ስለሰራሠተኞች መልቀቅ ጠይቀናቸው በሰጡት ምላሽ፤ ሠራተኞች በጡረታና በህልፈት እንጂ ሌላ የሚለቁበት ምክንያት እንደሌለ አመልክተው፤ ሌሎች የሚለቁበትን ምክንያቶች በተመለከተ ቢሮ ተገኝታችሁ ሠነዶችን በማየት ማረጋገጥ ይቻላል በሚል ምላሽ ሰጥተውናል፡፡

Read 3245 times