Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Monday, 07 November 2011 13:34

ሜሲ በፊፋ የሽልማት ሃትሪክ ተጠበቀ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ፊፋ የ2011 የዓለም እግር ኳስ ኮከቦችን ለመምረጥ ለሚያካሂደው ምርጫ የቀረቡ እጩዎችን ሰሞኑን አሳወቀ፡፡ በአሸናፊነት የሚመረጡት ኮከቦች ከ3 ወር በኋላ በዙሪክ በሚካሄድ ስነስርዓት የሚሸለሙ ሲሆን በ7 የሽልማት ዘርፎች ዕጩዎቹ ለዓመቱ ኮከብ ተጨዋችነት በወንዶች 23 ተጨዋቾች እጩ ሆነው ሲቀርቡ 3ኛ አሸናፊውን በሚፈልገው የዓለም ምርጥ አሰልጣኝ ምርጫ ላይ 10 ምርጥ አሰልጣኞች የሚወዳደሩ ይሆናል፡፡ የባርሴሎናው ሊዮኔል ሜሲ የክብር ሽልማቱን ለ3ኛ ግዜ በመውሰድ ልዩ ሃትሪክ መስራቱ ከወዲሁ የተረጋገጠ ይመስላል፡፡በፊፋ የዓለም ኮከብ ተጨዋች ምርጫ ታሪክ በተለያዩ ዓመታት 3 ጊዜ ማሸነፍ የቻሉት ቫንባስተን፤ክሩፍ፤ ፕላቲኒ፤ ሮናልዶና ዚኒዲን ዚዳን ናቸው፡፡

በ3 ተከታታይ ዓመታት አከታትሎ ያሸነፈው ብቸኛው ሰው አሁን የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ፕሬዝዳንት የሆነው ሚሸል ፕላቲኒ ነው፡ ከቀረቡት እጨዎች ባርሴሎና 8 ሪያልማድሪድ 5 በማስመዝገብ ቀዳሚ ናቸው፡፡ የባርሴሎናው አልቬስ፤ የሳንቶሱ ኔይማር፤ የሲቲው አጉዌሮ፤ የሊቨርፑሉ ሱዋሬዝን ያካተተው ዝርዝር ውስጥ ብቸኛው አፍሪካዊ በራሽያ ያለው ኤቶ እና ብቸኛው እንግሊዛዊ ሩኒ ሆነዋል፡፡ የአርሰናሉ ቫን ፐርሲ ሳይመለመል ቀርቷል፡፡ እጩ ሆነው ከቀረቡት አሰልጣኞች መካከል የባርሴሎናው ጋርዲዮላ፤ የማን ዩናይትዱ ሰር አሌክስ ፈርጉሰን፤ የአርሰናሉ አርሴን ቬንገር የቼልሲው ቪላስ ቦአስ የአምናው አሸናፊ የሪያል ማድሪዱ ሞውሪንሆ ይገኙበታል፡፡

 

Read 3695 times Last modified on Monday, 07 November 2011 13:39