Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Print this page
Monday, 07 November 2011 13:21

መድሃኒዓለም ት/ቤት 80ኛ ዓመቱን ያከብራል “ቁምነገር” ተማሪዎች አስመረቀ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

በሐገሪቱ ከመጀመርያዎቹ ትምህርት ቤቶች ተርታ የሚሰለፈውና ቀድሞ ባላባት ትምህርት ቤት በመባል የሚታወቀው የመድሃኒዓለም መሰናዶ ትምህርት ቤት የተመሠረተበትን ሰማንያኛ ዓመት ዛሬ እና ነገ ያከብራል፡፡ ጉለሌ አካባቢ የሚገኘው ትምህርት ቤት ሰማንያኛ ልደቱን የሚያከብረው በሙዚቃ እና በስፖርት ዝግጅቶች ሲሆን በዚሁ ዝግጅት ከትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ እና ጥሪ ከተደረገላቸው እንግዶች በተጨማሪ የትምህርት ቤቱ የቀድሞ ተማሪዎች ይገኛሉ፡፡ ከነዚሁ የቀድሞ ተማሪዎች መካከል የ94 ዓመት የእድሜ ባለፀጋ ይገኙበታል፡፡ በት/ቤቱ ከተማሩ የቀድሞ ተማሪዎቹ መካከል ኢንስትራክተር መንግስቱ ወርቁ፣ አርቲስት ዘርይሁን የትምጌታ፣ ካፒቴን አለማየሁ አበበ፣ አንጋፋው ሙዚቀኛ ሙላቱ አስታጥቄ፣ የዓለም ሎሬት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ ይገኙበታል፡፡

በሌላም በኩል “ቁምነገር የጋዜጠኞች ማሰልጠኛ ማዕከል” ለሦስትና ለስድስት ወራት በጋዜጠኝነት ያስተማራቸውን 35 ተማሪዎች ትናንት ካዛንቺስ በሚገኘው የ”ቁም ነገር” መፅሄት ቅጥር ግቢ ውስጥ አስመረቀ፡ የተግባር ልምምድ ያደረጉት አማተር ጋዜጠኞች በማሰልጠኛውና በታዋቂ ጋዜጠኞች ትምህርት ተሰጥቷቸዋል፡፡ በዜናና ፊቸር አፃፃፍ፣ በፕሬስ ሕግና በሌሎች አርእስትም ትምህርታቸውን እንደተከታተሉ ለማወቅ ተችሏል፡፡

Read 3598 times

Latest from