Print this page
Saturday, 16 March 2013 11:57

የግጥም ጥግ

Written by  -ገዛኸኝ ፀ-
Rate this item
(7 votes)

አንተ “ኩሩ” ህዝብ!
የዘራኸው መክኖ፣
የተከልከው ተመናምኖ፣
ቁልቁለቱን ተያይዘኸው
ሥልጣኔህ ታፍኖ… ሦስት ሺህ
ዘመን ኖረኻል፣
እየተራብክ “ተመስጌን” ሥትል፣
እውነቴን ነው ተናዶብሃል፡፡
ዓምላክህን ብትጠይቀው በመክሸፍህ
አዝኖብሃል፡፡
በተለይ አባባልህን፣ እንደ በቀቀን
እየደገምክ፣
“እከክ የሰጠ ዓምላክ፣ ጥፍር አይነሳም”
እያልክ፣
በሀገር በቀል ፍልስፍናህ፣ ውድቀትህን
በሚያራባው፣
ድግምትህን እንዲለፍፍ፣
ብላቴናውን ስታግባባው
ዓምላክ ታዝቦህ ኖሮ፣ እጅግ በጣም
ታሞብሃል፣
“ከውድቀቱ የተቋተ ህዝብ”
የትም አላየሁም ብሎሃል፡፡
የሆድህን ፎከት አይቶ፣ የአህያ እርሻ
ቢመስለውም፣
“እከክና”፣ እና “ጥፍር” እንዳልሰጠ
እሱም ቀድሞም አላጣውም፡፡
በተረትህ ውስጥ እንደሟሸሽክ
መቼም “ፈጣሪህ” አይጠፋውም፡፡
አንተ ግን አሁንም - እንደ እንግዴ ልጅ
በድነሃል፣
ስለ እከክህ ሳትጠይቅ፣ በጥፍርህ
“ተመስጌን” ብለሃል፡፡
“እውነት እውነትም--” ይልሃል!
(ድንገት ግን --)
አንጐልህን ማከክ ሲሳንህ፣ የጥፍርህ
ባዶነት ይገባኻል፡፡
ባምላክህ ብታሳብብም፣ እርግጥ ነው
እከክ ወርሰኻል፡፡
እውነት ነው፣ጥፍርህ ዶልዱሞ
እከክህ ብቻ ታምሷል፤
ይልቅ በላብህ፣ አጥበህ አንፃው
የንሰሃህ ዘመን ደርሷል፡፡

 

Read 3761 times