Saturday, 09 March 2013 12:22

...ጋብቻህን/ሽን ከመፍረስ አሁኑኑ አድን/ድኚ...

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ (ከኢሶግ)
Rate this item
(7 votes)

በአንድ ወቅት አንድ ሰውዬ እጅግ ተበሳጭቶ መንገድ መንገዱን እያወራ ሲሄድ አገኘሁት፡፡ እኔም #ምን ሆንክ ወንድሜ› አልኩና ጠየቅሁት፡፡ .ምን..vKu?‚ ካልተፋታን እያለች በጣም አስቸገረችኝ ...መቆሚያ መቀመጫ አሳጣችኝ አለኝ፡፡ እኔም ወደ አንድ ቡና መጠጪያ ቤት ይዤው ጎራ አልኩና ይኸውልህ... ነገሩ እንዲህ ነው ብዬ ማድረግ የሚገባውን እና አስፈላጊውን ነገር ሁሉ አጫወትኩት፡፡ ከዚያም በሌላ ቀን ሆን ብሎ ጠብቆ እንዲህ አለኝ፡፡ ወንድሜ ሆይ ያልከኝን ነገር በሙሉ አደረግሁ፡፡ ከዚያም ባለቤተ፤ ቁጭ ብላ ታዳምጠኝ ከነበረበት የአልጋችን ግርጌ ተፈናጥራ ተነስታ ዝም ብላ ትመለከተኝ ጀመር፡፡ እስቲ ድገምልኝ...ምን አልከኝአለችኝ፡፡ እኔም ያው በቃ...ያልኩሽን ነገር ከተረዳሽኝና ማመዛዘን ከቻልሽ ...የምትፈልጊው ሁሉ ይፈጸማል...መፋታት...ወይንም አብሮ መኖርአልኩዋት፡፡ ትንሽ ወዲያና ወዲህ ካለች በሁዋላ .ትሰማለህ...በምንም ምክንያት ትዳራችን አይፈርስም፡፡ አብረን መኖር ነው ያለብን፡፡

ይኄ ደግሞ ለማንም ሲባል ሳይሆን እኔ ለአንተ...አንተም ለእኔ አስፈላጊ ስለሆንን ብቻ ነው...ሌላው ነገር ከዚያ በሁዋላ ነው.. አለችኝ፡፡ በጣም አመሰግንሀለሁ...አሁን የእንፋታ ወሬ በቤተ፤ የለም.....አለኝ፡፡ ..ማንኛውም ሰው ነገርን ማለዘብ ከቻለ ትዳርን ለመበተን ሊተኮስ የተዘጋጀውን ጠብመንጃ ወደመሬት በመክተት ነጭ ባንዲራን ማውለብለብ ይቻለዋል፡፡. HOMER MCDONALD ለርእስነት የተጠቀምንበትን አባባል የተናገሩት (HOMER MCDONALD) ናቸው፡፡ ከርእሱ ቀጥሎ ያለው እማኝነትም የእሳቸው ነው፡፡ እኝህ ሰው የሚሉት... ለ45 አመታት ያህል በሺዎች የሚቆጠሩ ተጋቢዎችን በማማከርና ፍቅራቸውን እንደገና በማጠናከር ትዳራቸውን እንዲቀጥሉ ያደረግሁ ስለሆንኩ ልምዴን አሰባስቤ መጽሐፍ በመጻፍ ለአንባቢዎች አቅርቤያለሁ ነው ፡፡ የላንቺና ላንተ አምድም ትዳርን ከብዙ አቅጣጫ ስለሚመለከተው ጽሁፉን በመጠኑ ለንባብ ብሎታል፡፡ ቤተሰብን በተገቢው መንገድ ለመምራት የሚያስችል ማህበራዊ ተቋም ነው፡፡` ሕጻናት በሚያስፈልገው መልኩ እንክብካቤ አግኝተው እንዲያድጉ የሚያስችል ነው፡፡

 ማለት አንድ ወንድና ሴት በፍቅር ተግባብተው አንድ ለአንድ ጸንተው በጤና እንዲኖሩ የሚያስችል ቤተሰባዊ ትስስር ነው፡፡  ከሚሰጠው ቤተሰባዊ ትስስር በመነሳት ለህብረተሰብ ለሀገር ልማት አስተዋጽኦ የሚያደርጉ ሰዎችን ማፍራት የሚያስችል ነው፡፡ ከላይ የተዘረዘሩትና ሌሎችም ትሩፋቶች የሚገኙበት ትዳር አለአግባብ ከፈረሰ ግን በተቃራኒው ውጤቱ በግልም ይሁን በቤተሰብ ደረጃ አስከፊ ይሆናል፡፡ በተለይም ለስነተዋልዶ ጤና እክል የሚሆኑ ነገሮችን መጋበዝ ቀላል ይሆናል፡፡ ... መጠጥ ፣ሲጋራ፣ ጫት፣ ከማያውቁት ሰው ጋር የግብረስጋ ግንኙነት ማድረግ ለመሳሰሉት በኑሮ ላይ የተዛባ ስርአት ለሚያስከትሉ ነገሮች መጋለጥን ያስከተላል፡፡ የተዘረዘሩትን ነጥቦች መሰረት በማድረግ ማክ ዶናልድ ትዳርን ጠበቅ ለማድረግና ለመፍረስ በሚንገዳገድበት ወቅት ለማዳን ቀጣዮቹን ምክሮች ለግሰዋል፡፡

ጋብቻን ማዳን ወይንም ፍቅርን እንደነበር ማቆየት ይቻላል፡፡ HOMER MCDONALD...ትዳርን ለማዳን ደረጃ በደረጃ ምን ማድረግ እንደሚገባ ማሳየት እችላለሁ ይላሉ፡፡ ምክንያቱም... ከጉዳዩ ጋር በተገናኘ ለ45 አመታት ያህል በሺዎች የሚቆጠሩ ትዳሮችን አንደነበሩ ለመመለስ ችያለሁና ብለዋል፡፡ አንድ ትዳር ወይንም የፍቅር ግንኙነት ምንም እንኩዋን ተስፋ ያጣ ቢመስል በጥንካሬ ግን የፍቅረኛን ተቃውሞ ማቆምና ኑሮን በሰላማዊ መንገድ መቀጠል ይቻላል፡፡ ጸሐፊው በመጽሃፋቸው ካሰፈሩዋቸው ዋና ዋና ነጥቦች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡፡ 1. ለተፋቃሪ ወይንም አንዱ ወገን ለሌላኛው መተማመኛ መስጠት፣ ቀደም ባለው ግንኙነት ላለመግባባት ምክንያት የሆኑትን ነገሮች ዳግመኛ ላለመፈጸም አንዱ ለአንዱ በእርግጠኝነት ቃል መግባት ወይንም መተማመኛ መስጠት ያስፈልጋል፡፡ ...ከአሁን በሁዋላ ወደቀድሞው ድርጊት አልመለስም...ዳግመኛ አልዋሽም...ከዚህ በሁዋላ ከሌላ ሰው ጋር አልማግጥም...የመሳሰሉትን ነገሮች በተናገሩት መሰረት መፈጸም ይገባል፡፡ 2. የማስመሰል ተግባርን ማስወገድ አንዳንድ ሰዎች ከልባቸው ባላመኑበት መንገድ የትዳር ተጉዋዳኛቸውን በማስመሰል ቃላት ለመደለል ሲጥሩ ይታያሉ፡፡ ለምሳሌ እየደጋገሙ እወድሀለሁ... እወድሻለሁ ...ማለትን እንደመጠቀሚያ መንገድ የሚፈጽሙት ሰዎች ይልቁንም የበለጠ በመካከል የተፈጠረውን ችግር ወደከፋ ሁኔታ ሲለውጡት ይስተዋላሉ፡

፡ስለዚህ ይላሉ ማክ ዶናልድ...መውደድን በተግባር ማሳየት እንጂ በአፍ ቢደጋግሙት ከአታላይነት ያስፈርጃል፡፡ 3. ራስን ለመከላከል ምክንያትን መፍጠር ፣ አንዳንድ ሰዎች ለሚሰሩት ስራዎች ሁሉ የተዘጋጀ ማብራሪያ ያላቸው ይመስላሉ፡፡ ይህን ያደረግሁት በዚህ ምክንያት ነው...ስለዚህ ምንም እንከን የለውም...አንተ ወይንም አንቺ ለመቀበል ስላልፈለግህ/ግሽ ነው እንጂ ከድርጊቱ ጋር የሚያያዝ ምንም ችግር የለም ...በማለት ሌላኛውን ወገን ለማስረዳትና እራስን ለመከላከል መታገል በኑሮ መካከል እንከን ይፈጥራል፡፡ ይልቁንም ይህ ስራ ችግር ያስከትላል ተብሎ በሌላኛው ወገን ሲገለጽ መደረግ የሚገባው...ኦ...እኔ እኮ ጥሩ ነገር ነው ብዬ ነበር...ለካንስ ችግር አለው? ትክክል ነው... በማለት ወደእርምቱ መመለስ ወይንም ደግሞ ምክንያታዊ ለመሆን ሲባል ሳይሆን በትክክል ጠቀሜታውን ማስረዳት ያስፈልጋል፡፡

አንድ ሰው ስህተት ሰርቶ እራሱን ለመከላከል የሚጣጣር ከሆነ ይበልጥ ስህተተኛ ይሆናል፡፡ 4.. ነገሮችን ምንነታቸውን ሳያረጋግጡ በመጥፎ መልክ መመልከት፣ ...ባለቤቴ፤ ጥሩ ሰው አይደለም/አይደለችም ...የአስተሳሰብ ችግር አለባት/አለበት ...ባለቤቴ ለሁሉ ነገር ተሟጋች ነው /ናት በማለት ወደመጥፎ ነገር በመፈረጅ መቀበል ፍጹም ስህተት ነው፡፡ ከላይ የተዘረዘሩት አራት ነጥቦች ሰዎች ሊያደርጉዋቸው እንደማይገባቸው ቢያውቁም ነገር ግን ባህርይን ለማስተካከልና ሁኔታዎችን በበጎ ለመቀበል ወይንም ለእራስ እና ለአፍቃሪ ወገን ታማኝነትን ለመግለጽ እየተቸገሩ የሚፈጽሙዋቸው ነገሮች ናቸው፡፡ ጋብቻህን /ጋብቻሽን ከመፍረስ አሁኑኑ አድኚ/አድን የሚለውን መጽሐፍ የጻፉት ማክ ዶናልድ ለመፍትሔው ሶስት ነጥቦችን ጠቁመዋል፡፡ 1. ግፊት ማድረግን አቁም/አቁሚ፡፡ ተጋቢዎች ወይንም ፍቅረኛሞች አንዱ በሌላው ላይ የሚያደርጉትን ጫና ወይንም ግፊት፣ ማማረር፣ ነገርን ማውጠንጠን ማቆም አለባቸው፡፡ አንድ ሰው ያልፈለገውን ነገር እንዲያደርገ ወይንም የፈለገውን ነገር ከማድረግ እንዲታቀብ ግፊት ማድረግ በግንኙነት መካከል ችግርን ያስከትላል፡፡

በተጨማሪም በተደረገ ነገር ላይ ተመስርቶ ጭቅጭን መፍጠር አሊያም አንተ እኮ ወይንም አንቺ እኮ እንዲህ አድርገሽ/አድርገህ እያሉ ነገርን በማውጠንጠን ቀናትን መፍጀት እጅግ አስቸጋሪ ስለሆነ ትዳርን ወደአደጋ ሊጥለው ይችላል፡፡ 2. በሚደረጉ ነገሮች መስማማት፣ ተጋቢዎች በሚደረጉ ነገሮች እርስ በእርስ በመጨቃጨቅ ጊዜያትን ከመፍጀትና ወዳልታሰበ አቅጣጭ ሁኔታዎችን ከመምራት ይልቅ ሆን ተብሎም ይሁን ባልታሰበ መንገድ የተፈጠሩ ነገሮችን በስምምነት ማለፍ እና ለወደፊት ግን ተመካክሮ መፈጸም እንደሚረዳ በቅንነት ለአድራጊው ሰው መግለጽ የጋራ መግባባትን ይፈጥራል፡፡ 3. ደስታን በትክክለኛው መንገድ መግለጽ፣ በአለም አቀፍ ደረጃ አንድ የጋራ መግባቢያ መንገድ አለ፡፡ እሱም ...በእርግጠኝነት መደሰት...የራስን ጊዜ በተገቢው አጣጥሞ መጠቀም...በግል ነጻነት መደሰት...ሰዎች በጣም ኮስታራ ወይንም ፈጣን ቢሆኑብህ እራስን አሳምኖ መቀበል እና ትክክል እንደሆኑ መግለጽ ወይንም አለመንቀፍ የሚሉ እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡ ስለዚህ ተጋቢዎች በማናቸውም ነገር ደስታቸውን ሲገልጹ በእርግጠኝነት ሊሆን ይገባዋል፡፡ ካለበለዚያ ባልተደሰቱበት ነገር የተደሰቱ በመምሰል ስሜታቸውን ለመግለጽ ቢሞክሩ በግል እራሳቸውን ከመጉዳታቸው በተጨማሪ ትዳራቸውንም ጉዳት ላይ ይጥሉታል፡፡

ከላይ የተገለጹትን ነገሮች በእለት ወይንም በሳምንት ላትፈጽመው/ላትፈጽሚው ትችያለሽ/ላለህ፡፡ ነገር ግን እነዚህንና ሌሎች ነገርን ለማለዘብ የሚረዱ ነገሮችን ለመጠቀም ጊዜ ወስዶ እራስን በማሳመን ወደተግባር መቀየር ይቻላል፡፡ ማንኛውም ሰው ነገርን ማለዘብ ከቻለ ትዳርን ለመበተን ሊተኮስ የተዘጋጀውን ጠብመንጃ ወደመሬት በመክተት ነጭ ባንዲራን ማውለብለብ ይቻለዋል፡፡ ይህን ያደረገ ሁሉ ትዳሩን ከመበተን ሊያድን ይቻለዋል፡፡ ብለዋል ጸሐፊው HOMER MCDONALD፡፡

Read 5248 times