በሶሻል ሚዲያ መድረኮች ጀስቲን ቢበር ባለው እውቅና ከኦባማና ከዳይላማ መብለጡን ያመለከተው ዘ ኦብዘርቨር ጋዜጣ፤ በፌስቡክ 36 ሚሊዮን አድናቂዎች፤ በትዊተር ደግሞ 13 ሚሊዮን ተከታዮችን እንዳፈራ ጠቅሷል፡ በዩቲውብ ከሚታዩ የቪድዮ ምስሎች የዘመኑ ምርጥ ድምፃውያን 86 በመቶ ድርሻ እንደያዙ የጠቆመው ጋዜጣው፤ በየሁለት ቀኑ የ48 ሰዓታት የቪድዮ ምስሎች የሚጫንበት የአርቲስቱ ድረገፅ በየቀኑ 3 ቢሊዮን ተመልካች ይጎበኘዋል፡፡ ጀስቲን ቢበር እድሜያቸው ከ30 በታች ከሆኑ ዝነኞች በሚያገኘው የክፍያ መጠን ሁለተኛ ደረጃ መያዙን ያመለከተው ፎርብስ መፅሄት በበኩሉ ባለፉት 12 ወራት 53 ሚሊዮን ዶላር መስራቱን አስታውቋል፡፡ በ3ዲ የተሰራው “ጀስቲን ቢበር፡ ኔቨር ሴይ ኔቨር” የተሰኘው ጥናታዊ ፊልሙ የ100 ሚሊዮን ዶላር ትርፍ ማስገኘቱ ለገቢው ማደግ ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳበረከተ ታውቋል፡፡