Sunday, 03 March 2013 00:00

በ150 ሚ. ብር የተገነባው ‹‹አዶላላ ሪዞርት›› ሊመረቅ ነው

Written by  አበባየሁ ገበያው
Rate this item
(0 votes)

በቢሾፍቱ ከተማ በባቦጋያ ሃይቅ ዙሪያ በትውልድ ኢትዮጵያዊ በዜግነት ሩሲያዊ በሆኑት ዶ/ር አስራት ለገሰ ባለቤትነት በ150 ሚ ብር ወጪ የተገነባው “አዶላላ ሪዞርት” በሚቀጥለው እሁድ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል፡፡
የአዶላላ ሪዞርት ሃምሳ ደረጃቸውን የጠበቁ የመኝታ ክፍሎች፤ የስፖርትና የመዝናኛ ማዕከሎች ያሉት ሲሆን በምረቃ በዓሉ ላይ ጠ/ሚ ሃይማርያም ደሳለኝን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እንዲሁም የሩሲያ የነዳጅ ኩባንያ ባለሃብቶች፣ ኢትዮጵያ ውስጥ በሆቴልና በማዕድን ዘርፍ ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ ኢንቨስት ለማድረግ እየተንቀሳቀሱ ያሉ ሩሲያዊ ባለሃብቶች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል። የአፍሪካ ህብረት ከፍተኛ ባለስልጣናት ምእንደሚገኙ ተጠቁሟል፡፡
ከ32 አመታት በፊት ወደ ሩሲያ ለትምህርት የሄዱትና ኑሯቸውን በሞስኮ ያደረጉት ዶ/ር አስራት ለገሠ፤ እ.ኤ.አ. በ1990ዎቹ መጀመሪያ በሩሲያ ውስጥ በ5ሺ ዶላር የጀመሩትን ቢዝነስ በማስፋፋት የሰባት ባርና ሬስቶራንቶች ባለቤት ለመሆን ችለዋል፡፡ ባለሃብቱ ከስድስት ዓመት በፊት ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ የኢንቨስትመንት ፈቃድ አውጥተው በቢሾፍቱ ከተማ በባቦጋያ ሀይቅ ዙሪያ በ70ሺ ስኩዌር ካሬ ሜትር ላይ ያረፈውን “አዶላላ ሪዞርት” ገንብተዋል፡፡
ዶ/ር አስራት በሩሲያ የፒኤችዲ ኬሚካል ኢንጅነሪንግ ምሩቅ ሲሆኑ ከሩሲያዊት ሴት ጋር ትዳር መስርተው ልጆች አፍርተዋል፡፡
ከዶ/ር አስራት ለገሠ ጋር ያደረግነውን በአስገራሚና ድንቅ ታሪኮች የተሞላ ቃለምልልስ በሚቀጥለው ሳምንት እናቀርባለን፡፡

Read 3498 times