የሩሲያዊው ሐኪምና ደራሲ የአንቶን ቼሆቭ 153ኛ የልደት በዓል የፊታችን ሰኞ ከቀኑ 11 ሰዓት ጀምሮ በፑሽኪን አዳራሽ በሙዚቃ ዝግጅት እንደሚከበር የሩስያ የሳይንስና የባህል ማዕከል አስታወቀ፡፡ በዕለቱ የሩስያ የፒያኖ እና የኦፔራ ሙዚቀኞች ናታሊያ ኮርሹኖቫ እና አሌክሲ ፓርፌኖቭ ሥራዎቻቸውን ለታዳሚው ያቀርባሉ ተብሏል፡፡“ሥነፅሁፍ ውሽማዬ ሕክምና የሕግ ሚስቴ” ይል የነበረው ሩስያዊው ሐኪምና ደራሲ አንቶን ቼሆቭ፣ ሩስያ ካፈራቻቸውና ሥራዎቻቸው በዓለም ዙርያ ከናኙ የአጭር ልቦለድ ፀሐፍት አንዱ ነው፡፡ የሰኞ አመሻሹ ዝግጅት በሩስያ የባህላዊ ሻይ አፈላል (ሳሞቫር) የሚታጀብ ሲሆን ለታዳሚዎች የሻይ ግብዣ እንደሚኖር የባህል ማዕከሉ ጠቁሟል፡፡
Published in
ኪነ-ጥበባዊ ዜና
Latest from Administrator
- የእስራኤል እና የኢራን ፍጥጫ
- Insights on Israel's Response: Interview with Mr. Tomer Bar-Lavi, Chargé d’Affaires at the Embassy of Israel to Ethiopia
- Barr, a vocal Trump critic, says he will ‘support the Republican ticket’ in November
- Iran president warns of ‘massive’ response if Israel launches ‘tiniest invasion’
- "አልሞቷል" ፊልም ዛሬ በዓለም ሲኒማ ይመረቃል