Print this page
Saturday, 09 February 2013 10:44

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ተከላከል ተባለ

Written by  ዓለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(0 votes)

አዲስ ታይምስን በተመለከተ ወደ ፍርድ አመራለሁ ብሏል የሕዝብን ሐሳብ ማናወጥ፣ሕዝቡን በሕገ-መንግስቱ ላይ ማነሳሳትና የመንግስትን ስም በማጥፋት ሦስት ክሶች ክስ የቀረበበት የፍትሕ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳኝለኝ እንዲከላከል ፍርድ ቤቱ ወሰነ፡፡ ማስተዋል አሣታሚ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር በበኩሉ እነዚህን ዕትም በማውጣት በሚል የቀረበበትን ክስ በተመሳሳይ እንዲከላከል ተወስኖበታል፡፡

ተከሳሾች ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እና ማስተዋል አሳታሚ የመከላከያ ማስረጃቸውን እንዲያቀርቡ ለመጋቢት 17ቀን 2005 የከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 16ኛ ወንጀል ችሎት በትናንትናው ዕለት ወስኗል፡፡ በተያያዘም የአዲስ ታይምስ መጽሔት አሣታሚ የሆነው ኢዱ ሕትመትና ማስታወቂያ ኃላፊቱ የተወሰነ የግል ማኅበር በቀጣይ ሣምንት የመጽሔት እድሳት ፍቃዱን በከለከለው በኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን ላይ ክስ እንደሚመሠርቱ የመጽሔቱ ማኔጂንግ ኤዲተር አቶ ተመስገን ደሳለኝ ለዝግጅት ክፍላችን ገልፀዋል፡፡

ክሱን ባሳለፍነው ሣምንት ባሉት ቀናት ለማቅረብ ከሕግ አማካሪ ጠበቃቸው ጋር ተመካክረው እንደነበር የተናገሩት አቶ ተመስገን ‹‹በአንዳንድ ምክንያቶች ለሚቀጥለው ሣምንት ለማስተላለፍ ተገድደናል›› ብለዋል፡፡ አሣታሚ ድርጅቱ ክስ የሚያቀርበው ከኢትዮጵያ መንግስት ፍትህን አገኛለሁ ብሎ ሳይሆን በክሱ ሂደት ላይ የሚታዩ እውነቶች ለታሪክና ለትውልድ ተመዝግበው እንዲቀመጡ በማሰብ እንደሆ አቶ ተመስገን ለአዲስ አድማስ አስታውቀዋል፡፡ ባለፈው ሣምንት “አዲስ ታይምስ መጽሔት ታገደ” በሚል ርዕሰ በወጣው ዜና ላይ “የአክስዮኑ 93 በመቶ ድርሻ ባለቤት አገር ውስጥ እንዳልሆኑ” የሚለው ‹‹ከአዲስ አበባ ወጪ ክፍለሀገር ይገኛሉ›› በሚለው ተስተካክሎ እንዲነበብ የዝግጅት ክፍላችን ይጠይቃል፡፡

Read 3402 times Last modified on Saturday, 09 February 2013 14:19