Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 12 January 2013 10:07

“ሴት የላከው” ፊልም በድጋሚ ይመረቃል

Written by 
Rate this item
(13 votes)

በደራሲ ኢንጂነር ግርማይ ኃይል ተፅፎ የተዘጋጀው “ሴት የላከው” የ97 ደቂቃ ፊልም ባለፈው ማክሰኞ የተመረቀ ሲሆን በእለቱ በነበረው የኤሌክትሪክ ሃይል መዋዥቅ የተነሳ ፊልሙ ሙሉ በሙሉ ባለመታየቱ በድጋሚ እንደሚመረቅ ቶኔቶር ፊልም ፕሮዳክሽን አስታወቀ፡፡ በእለቱ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ትያትር መሰል ችግር ስላልነበር ሙሉ ፊልሙን አሳይተናል ያሉት የፕሮዳክሽኑ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ግርማይ ኃይሌ፣ፊልሙ በታየባቸው ሶስት ቦታዎች ግን በኤሌክትሪክ ሃይል መዋዠቅ የተነሳ ለ58 ደቂቃ ብቻ ለማሳየት መገደዳቸውን ተናግረዋል፡፡

በሕፀፅ-ተቺ አስቂኝ ፊልሙ ላይ አንጋፋዋ አርቲስት ወለላ አሰፋ፣ ተሻለ ወርቁ፣ ትዕግስት አድነው፣ ግርማይ ኃይሌና ሌሎችም ተውነዋል፡፡ ቶኔቶር ሕዳር 18 ቀን 2005 ዓ.ም “ከካምፓስ ያሁኑ ይባስ” ፊልም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ትያትር ሲያስመርቅ፣በሳምንቱ ሕዳር 25 ቀን 2005 ዓ.ም “አንድ’ዜ” የተሰኘ ትያትር በተመሳሳይ ስፍራ ማስመረቁ ይታወቃል፡፡

Read 12191 times