ደራሲ ገስጥ ተጫኔ ካሁን ቀደም ዘነበ ፈለቀ በሚል ርእስ “ነበር” የተሰኘ ባለ ሁለት ክፍል መጽሐፍ፣ እንዲሁም “የናቅፋው ደብዳቤ”፣ “እናት ሀገር”፣ “የፍቅር ቃንዛ”፣ “የማክዳ ንውዘት” እና “የረገፉ ቅጠሎች” የተሰኙ መጻሕፍት ለንባብ አብቅተዋል፡፡ ደራሲው ከአዲስ አድማስ ጋር ባደረጉት የስልክ ቃለ ምልልስ ለሕትመት ዝግጁ የሆኑ ሌሎች መጻሕፍት እንዳሉዋቸውና በማሳተሚያ ገንዘብ እጥረት ሊያሳትሙት እንዳልቻሉ ገልፀዋል፡፡
በሌላ በኩል ደራሲ አብዱልበር ነስሮ የፃፈው “አነበብካት” የረዥም ልቦለድ መጽሐፍ ታትሞ ሰሞኑን ለንባብ ቀረበ፡፡
በፒስ ፕሪንቲንግ ፕሬስ ታትሞ ለንባብ የበቃው ባለ 166 ገፅ መጽሐፍ ዋጋ 49.99 ብር ነው፡፡
አብዱልበር ካሁን ቀደም “የቼዝ ምድር” የተሰኘ የግጥም እና የአጭር ልቦለድ መድበል አሳትሟል፡፡