Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 12 January 2013 10:06

ቢዮንሴ እና ሌዲ ጋጋ ነጠላ ዜማ ሊያወጡ ነው

Written by 
Rate this item
(3 votes)

ታዋቂዎቹ አቀንቃኞቹ ቢዮንሴ ኖውልስ እና ሌዲ ጋጋ ከሶስት ዓመት በኋላ በጋራ ነጠላ ዜማ ሊያወጡ እንደሆነ ተገለፀ፡፡ አርቲስቶቹ ለሚሰሩት አዲስ ነጠላ ዜማ ስቱድዮ መግባታቸውን የዘገበው “ዘ ዋየር”፤ ተመሳሳይ የጆሮ ጌጦችን ማድረግ መጀመራቸውንና ይሄንኑ የሚያሳዩ ፎቶዎች በማህበራዊ ሚዲያዎች ሲያሰራጩ መቆየታቸውን አመልክቷል፡፡ ነጠላ ዜማው በቀጣይ ወር ለገበያ እንደሚበቃ የሚጠበቀው የሌዲ ጋጋ ‹‹አርት ቶፕ› የተሰኘ አዲስ አልበም መሪ ዜማ እንደሚሆንም ታውቋል፡፡ ሁለቱ የፖፕ ሙዚቃ ንግስቶች ከሶስት ዓመት በፊት “ቴሌፎን” በተባለው ነጠላ ዜማ ከፍተኛ ተቀባይነት አግኝተው የነበረ ሲሆን በሌዲ ጋጋ ግጥም በተሰራው “ቴሌፎን” የተሰኘ ዜማ ላይ ቢዮንሴ በአጃቢነት አቀንቅናለች፡፡ ዜማው በመላው ዓለም 7.4 ሚሊዮን ዲጂታል ቅጂዎች እንደተሸጡ ይታወቃል፡፡

ኔልሰን ሳውንድ ስካን እንደገለፀው፤ በ2012 ዓ.ም የሙዚቃ አልበሞች፣ ነጠላ ዜማዎች፣ ክሊፖች እና ዲጂታል ዘፈኖች ጠቅላላ ሽያጭ ከ850 ሚሊዮን ዶላር በላይ ነበር፡፡ በዓመቱ በአልበማቸው ሽያጭ ስኬታማ ከሆኑት ድምፃውያን መካከል አዴሌ “21” በተባለ አልበሟ የመሪነት ደረጃውን ይዛለች - 3.7 ሚሊዮን ቅጂዎች በመሸጥ፡፡ ሊዮኔል ሪቼ “ታስኪጅ” የተባለ አልበሙን 912ሺ ቅጂዎች በመቸብቸብ ሁለተኛ ደረጃን የያዘ ሲሆን፤ ዋን ዲያሬክሽን “አፕ ኦል ናይት” የተባለ አልበማቸውን 818ሺ ቅጂዎች በመቸብቸብ ሶስተኛ ሆነዋል፡፡ በአዲሱ የፈረንጆች ዓመት በርካታ አዳዲስ አልበሞች እንደሚወጡ የገለፀው ቢልቦርድ መፅሄት፤ በጉጉት ከሚጠበቁት መካከልም የቢዮንሴ፤ የሌዲ ጋጋ፤ የቢበር፤ የኤምነም፤ የማርያ ኬሪ፤ የማይሊ ሳይረስ፤ የሊል ዋይኔ ዋና ዋናዎቹ እንደሚሆኑ ጠቁሟል፡፡

Read 10998 times