Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 12 January 2013 10:04

በአዲሱ ዓመት ምርጥ ፊልሞች ይጠበቃሉ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

በአዲሱ የፈረንጆች ዓመት በርካታ ምርጥ ተዋናዮችን ያሳተፉ ምርጥ ፊልሞች የዓለም ሲኒማዎችን እንደሚያጥለቀልቁ ተገለፀ፡፡ አክሽን ፊልሞች፤ በ3ዲ በድጋሚ የተሰሩ እንዲሁም ጥቂት የማይባሉ ሳይንሳዊ ልቦለድ ፊልሞች ከሚቀጥለው ወር ጀምሮ በተከታታይ እንደሚለቀቁ ይጠበቃል፡፡ ከፊልሞቹ መካከልም ብሩስ ዊልስ የሰራው “ጂአይ ጆ ሪታሊዬሽን”፣ የቶም ክሩዝ “ቶፕ ገን” እና የስፒልበርግ “ጁራሲክ ፓርክ” በአዲስ መልክ በ3ዲ፤ “አይረን ማን ሶስት” እና “ስታር ትሬክ ኢንቱ ዳርክነስ› ይጠቀሳሉ፡፡

በሌላ በኩል በ2012 ዓ.ም የፊልሞች አጠቃላይ ገቢ ከ33 ቢሊዮን ዶላር በላይ እንደነበር የገለፀው ቦክስ ኦፊስ ሞጆ፤ በሰሜን አሜሪካ ገቢው ከካቻምናው ከ6 በመቶ በላይ በመጨመር 10.8 ቢሊዮን ዶላር አስመዝግቦ አዲስ ክብረወሰን እንደያዘ አመልክቷል፡፡
በ2012 በዓለም ሲኒማዎች ለእይታ የበቁ ፊልሞች በቁጥር 655 ሲሆኑ 1.36 ቢሊዮን ተመልካቾች እንደተመዘገቡና በትኬት ሽያጭ ከባለፉት ዓመታት 5.6 በመቶ እድገት እንደታየ ተገልጿል፡፡

Read 6846 times