Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Print this page
Saturday, 12 January 2013 09:49

የቀልድ ጥግ

Written by 
Rate this item
(6 votes)

የ80 ዓመት አዛውንት ለጠቅላላ የጤና ምርመራ (Checkup) ሆስፒታል ይሄዱና ሃኪማቸው “እንዴት ነው ጤንነትዎ?” ሲል ይጠይቃቸዋል፡፡
ሽማግሌውም “በጣም ጤና ነኝ ---እንደውም የ18 ዓመት ኮረዳ አግብቼልህ አርግዛልኛለች----ልጅ ላገኝ ነው --- መታደል ነው አይደል?” ይሉታል - ለሃኪሙ፡፡ ሀኪሙ ነገሩ አልተዋጠለትምና ትንሽ ሲያስብ ከቆየ በኋላ “አንድ ታሪክ አስታወሱኝ” በማለት ይነግራቸዋል፡፡
“አንድ እኔ የማውቀው አደን የሚወድ ሰውዬ ነበር፡፡ በቃ የአደን ነገር ጨርሶ አይሆንለትም፡፡

አንድ ቀን ለአደን ሲወጣ ታዲያ ጠብመንጃውን አነሳሁ ብሎ ዣንጥላውን ይዞ ይወጣል፡፡ ገና ጫካ ውስጥ እንደገባም ከየት መጣ ሳይባል አንድ የተበሳጨ ድብ ፊትለፊቱ ገጭ ይልበታል፡፡ ከመቀፅበት ዣንጥላውን እንደጠመንጃ አስተካክሎ ድቡ ላይ ያነጣጥርበትና እጀታውን ይጫነዋል----ድቡ ወዲያው መሬት ላይ ጠብ ይላል” አላቸው ሃኪሙ፡፡
ሽማግሌውም “ይሄማ ሊሆን አይችልም! ድቡ ላይ የተኮሰው ሌላ ሰው መሆን አለበት!” አሉ - ጮክ ብለው፡፡
ሀኪሙም “የእርስዎም ነገር እኮ እንደዚያ መስሎኝ ነው” አላቸው፡፡

Read 9523 times

Latest from