Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Print this page
Saturday, 12 January 2013 09:47

በነገራችን ላይ

Written by 
Rate this item
(3 votes)

ነ.መ.
በነገራችን ላይ ማለት፣ ሁሉን ጐራሽ ሀረግ ሆኗል
ኑ መቃብር እንለካካ፣ ብሎ መጀመር ይቻላል
ኑሮን እንይ ከማለት፣ ሞትን መግለጽ ይቀላል፡፡
በነገራችን ላይ፤
ገዳይ በግፍ ገሎ ሳለ
ሟች ይጠየቅ ከተባለ
ገና ዕዳችን አላለቀም የባሰም ሌላ ግፍ አለ
ከሬሳችን የከበደ፣ ከህሊና የቀለለ!!
በነገራችን ላይ …
ከሟች የተረፈ እንዳለ
ከገዳይም ተራፊ አለ፡፡

ታሪክ ምን እንደሚፈርድ፣ ባናቅ የዕጣ ፈንታን ጉዳይ 
እርግጡ ግን አንድ ነገር፣ አንዱ ሟች ነው አንዱ ገዳይ!
በነገራችን ላይ…
ለአንዳንዱ፤
መቼም ዘመን ሽለ - ሙቁ፣ ምን አይወሠደው ጉድ አለ?
ሞቻለሁ ቢልሳ ምን ግዱ፣ ሞቱ ለቤሣ ከዋለ
ቀብሩን የሚለካ እንጂ፣ ኑሮ እሚመትር ሲጠፋ
የቁም ሙቱ እየበዛ፣ መቃብር አፉ ሲሰፋ
መማማሩ መቻቻሉ፣ ከቂም በትር ካላዳነን
የትጋ ነው የነግ ተስፋችን?!
ለሞታችን በሞት መካስ፣ ከሆነ መጪ ደስታችን
ይሙቱ ካሉን ገዳዮች፣ ዕምኑ ላይ ነው ብልጫችን?!
የዛሬ መቃብርኮ በስክ ቢተኙም አይበቃ
መሬቱ ተቸርችሮ አልቋል፣ ቆሞ መሞት ነው በቃ?
በቁም መቀበር ነው በቃ
ነግ መቃብር እንዳታጣ፣ በጊዜ ሙት ያሉት ለካ
ወደው አደለም አበሾች፣ ኑሮ ተሳካ አልተሳካ!
በነገራችን ላይ…
እያደር ይሞላል ያልኩት፣ ያፈሳል እንዴ ታሪኩ
ሽንቁር አለው ወይ ትውልዱ፣ የዕውነት የት ነው ውሃ - ልኩ?!
በነገራችን ላይ …
“ካደረ አያገለግል”፣ እንዳሉት የነጋዴ ዕቃ
አድረን አንታይም አልን፣ ተርፈን ኖረን ስናበቃ
ይሄው ነው መርገምቱ በቃ!
የቁም ሙት እየወፈረ
ቁመቱም እየጨመረ
የዕውነት ሟች ከርሞ እየከሳ
ስሙም መልኩም ጥቅሙም ሳሳ፡፡
ኑ መቃብር እንለካካ፣ ርዝመት - ዕጥረቱ ይታወቅ
ከየለት ግፋችን ጋራ፣ ታስቦ ይመዘን በሀቅ!
ከኑሮ መሻሻል ይልቅ፣ መቃብር ማማረጥ መርጦ
መቼም መኖር መሞት ሆኗል፣ ውሸትን ከዕውነት
ሸምጥጦ ዋጋ ካወጣ ምን ገዶ
በመኖር መሞት ተለምዶ!


Read 6583 times

Latest from