Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 05 January 2013 11:49

በዓመቱ የኮንሰርት ገቢ ማዶና ትመራለች

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

በዘንድሮ የፈረንጆች ዓመት የኮንሰርት ገቢ የፖፕ ሙዚቃ ንግስቷ ማዶና በአንደኝነት እንደምትመራ ፎርብስ መፅሄት አስታወቀ፡፡ ሊጠናቀቅ ሁለት ቀናት ብቻ በቀረው 2012 ዓ.ም ሙሉ ለሙሉ ትኬታቸው የተሸጡ 72 ኮንሰርቶችን በመላው ዓለም ያደረገችው ማዶና፤ በአጠቃላይ 1ሚ.635ሺ176 ታዳሚዎችን በማዝናናት 228.4 ሚ. ዶላር ገቢ አድርጋለች፡፡

ብሩስ ስፕሪንግስተንና እና “ዘ ስትሪት ባንድ” በበኩላቸው፤ 72 ኮንሰርቶች ላይ በመስራት 199.4 ሚ. ዶላር አስገብተው በሁለተኛ ደረጃ ሲቀመጡ፤ ሮጀር ዋተርስ በ72 ኮንሰርቶች 186.5 ሚሊዮን ዶላር ገቢ በመሰብሰብ ሶስተኛ ደረጃ አግኝቷል፡፡ በቢልቦርድ የሙዚቃ የገበያ ሰንጠረዥ ተቀናቃኝ ያጣችው አሜሪካዊቷ ቴይለር ስዊፍት፤ እስከ 10ኛ ባለው ደረጃ ሳትገባ መቅረቷ አስገርሟል፡፡ 183 ኮንሰርቶች በመላው ዓለም የቀረቡበት የማይክል ጃክሰን “ዘ ኢሞርታል ዎርልድ ቱር” 147.3 ሚ. ዶላር፤ ኮልድ ፕሌይ 147.3 ሚ. ዶላር፤ ሌዲ ጋጋ 124.9 ሚ. ዶላር፤ ኬኒ ቼዝኒ እና ቲም ማክግሩው 96.5 ሚ. ዶላር፤ ቫን ሄለን 54.4 ሚ. ዶላር፤ ጄይዚ እና ካናዬ ዌስት 47 ሚ. ዶላር እንዲሁም አንድሬ ሬው 46.8 ሚ. ዶላር ገቢ በሰሩት ኮንሰርቶች በማስገባት እስከ 10ኛ ያለውን ደረጃ እንደወሰዱ ፎርብስ አመልክቷል፡፡

Read 4888 times