Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 29 December 2012 08:38

ዶ/ር ሀይሉ ከሃላፊነት የለቀቅኩት ታምሜ አይደለም አሉ Featured

Written by 
Rate this item
(3 votes)

የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ የነበሩት የ66 አመቱ ዶ/ር ሀይሉ አርአያ ከሃላፊነት የለቀቅኩት በህመም ሳይሆን ስልጣን ለወጣቱ ትውልድ ለማስተላለፍ ነው አሉ፡፡
ለህክምና ወደ አሜሪካ መሄዳቸውን ተከትሎ ለህይወታቸው የሚያሰጋ ህመም እንደገጠማቸው፣ የደም ካንሠር እንደተገኘባቸው እና ሌሎች ወሬዎች ሲናፈሱ እንደቆዩ የጠቆሙት ዶ/ር ሀይሉ፤ ሁሉም ከእውነት የራቁ እንደሆኑና በሙሉ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ለአዲስ አድማስ ገልፀዋል፡፡

ከፓርቲው ሀላፊነታቸው የለቀቁትም በህመም ሳይሆን የተሻለ ስራ ለመስራትና ጠንካራ ለውጥ ለማምጣት ከእኛ ይልቅ ወጣቶቹ ይሻላሉ በሚል እንደሆነ ገልፀዋል፡፡ ምክትላቸው ለነበረው ወጣት ዳንኤል ተፈራ ስልጣናቸውን ሲያስረክቡ ከእሳቸው የበለጠ በመንቀሳቀስ የተሻለ ነገር እንደሚሰራ በማመን እንደሆነም ይናገራሉ - ዶ/ር ኃይሉ፡፡ የፓርቲው ሃላፊነታቸውን ቢለቁም በብሔራዊ ምክር ቤት አባልነታቸው እንደሚቀጥሉ የጠቆሙት ዶ/ር ኃይሉ፤ ከትግል የሚለየኝ ሞት ብቻ ነው ብለዋል፡፡ 
አንዳንድ ሠዎች ምን እየሠራችሁ ነው እያሉ ይጠይቁናል ያሉት ዶ/ር ሀይሉ፤ የትግሉ ባለቤት ህዝብ ስለሆነ እያንዳንዱ ሰው ምን እየሠራሁ ነው ብሎ እራሱን መጠየቅ አለበት - ብለዋል፡፡
ፓርቲዎች ሃላፊነታቸው ትግሉን ማጠናከርና ማስተባበር እንደሆነ በጠቆምም አሁንም በርካታ ለትግል የሚያነሳሱ ችግሮች ስላሉ ህዝቡ በሠላማዊ ትግል ውስጥ በመሳተፍ ለውጥ እንዲያመጣ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡

Read 5734 times Last modified on Saturday, 29 December 2012 08:46